Tuesday 9 April 2013

በጉዲፈቻ ስም ህጻናትን መሸጥ እንደቀጠለ ነው


ECADF News – ኢትዮጵያ ዉስጥ ህጻናትን በጉዲፈቻ ስም ለፈረንጆች አዘጋጅተው ከሚያቀብሉት የንግድ ድርጅቶች አንዱ “እናት አለም ወላጅ አልባ ህጻናት” ወይም “Enat

Adoptions from the the Enat Alem orphanage in Ethiopia. Alem orphanage” ቀደም ሲል ድርጅቱ ህጻናቱን ምግብ በመከልከል፣ ሲታመሙ ተገቢውን ህክምና ባለመስጠትና በአጠቃላይ ለህጻናቶቹ እንክብካቤ ባለማድረግ ስሙ የተነሳ ሲሆን… አሁን ደግሞ የተገኙት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ድርጅቱ ድሀ እናቶችን እያፈላለገ ልጆቻቸውን “በእናት አለም ወላጅ አልባ ህጻናት” በኩል ጉዲፈቻ እንዲሰጡ እንደሚያግባባ ተደርሶበታል።
ከድርጅቱ ሰራተኞች አንዱ ግርማ ቀበለ በ“እናት አለም ወላጅ አልባ ህጻናት” የጥበቃ ሰራተኛ ሲሆን ለሲውዲን ጋዜጠኞች እንደተናገረው… ሌሊቱን በየመንደሩ እየተዘዋወረ ደሀ እናቶች ልጆቻቸውን ለፈረንጆች ጉዲፈቻ እንዲሰጡ እንደሚያግባባና እስካሁን በ145 ጉዲፈቻዎች ውስጥ እጁ እንዳለበት ተናግሯል።

የወያኔ ባለስልጣናት ተሯሩጠው የተጋለጠውን ድርጅት ዘግተውታል፣ ይሁንና አብዛኞቹ በጉዲፈቻ ስም ህጻናትን ከድሀ እናቶች ላይ ወስደው በመሸጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ስውር የወያኔ ባለስልጣናት እጅ እንዳለባቸው ይጠረጠራል።
በርካታ የመብት ተሟጋች ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን አምርረው ያወግዙታል። ነዋሪነቱ በኖርዌይ የሆነው ሀያሲ (blogger) ጌታባለው በቀለ፣ ሰሞኑን “ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?” በሚል ርዕስ ባስነበበው ጦማሩ እንዲህ ብሎ ይጠይቃል “ሕፃናት አሳዳጊ የሚያጡት ባብዛኛው የርስበርስ ጦርነት ሲኖር ወይንም ሰላም በተናጋበት ጊዜ ነው። ኢትዮጵያ ግን ጎዳና የወጡት ሕፃናቶቿ የበዙት በአንፃሩም ቢሆን ጦርነቱ ከቆመ ጊዜ ጀምሮ ነው ለምን?”።
ከዚህ ቀደም የአውስትራሊያው “ABC News” ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ቅጥ ያጣ ጉዲፈቻ ባጋለጠበት ወቅት ድረ-ገጻችን ጉዳዩን ዘግቦ ነበር። ከጥቂት ወራቶች በሗላ በዋሽንግተን ዲሲ በሚኖሩ የወያኔ አባላት በኩል የተቀጠረ ጠበቃ “የጉዲፈቻ ድርጅቱን ስም በማጉደፍ” ድረ-ገጻችንን ለመክሰስ እየተሰናዳ መሆኑን አሳወቀን። ከጠበቃው ጋር በተነጋገርንበት ወቅት “ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ስላለው በጉዲፈቻ ስም ህጻናትን የመሸጥ ጉዳይ” በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች መነሳቱን እንደምንፈልገውና እንዲያውም የኢትዮጵያ ባለስልጣናትን የበለጠ ለማጋለጥ እንደሚረዳን አሳወቅነው ነበር። ይሁንና ጠበቃው በጉዳዩ ዙሪያ ተመልሶ አላነጋገረንም።

No comments:

Post a Comment