Thursday 18 April 2013

የኢትዮጵያና የአዉሮጳ ሕብረት መሪዎች ዉይይት


የአዉሮጳ ሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ማኑኤል ባሮሶ ዛሬ የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚንስትር ካነጋገሩ በሕዋላ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ዘላቂነት የሚኖረዉ ሠብአዊ መብት ሲከበር መሆኑን አስታዉቀዋል

አዉሮጳን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ዛሬ ብራስልስ-ቤልጅግ ዉስጥ ከአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት ከማኑኤል ባሮሶ ጋር ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩን ትናንት ሽትራስ ቡርግ-ፈረንሳይ ዉስጥ ያነጋገሩት የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ማርቲን ሹልስ ዛሬ እንዳስታወቁት በትናንቱ ዉይይት ወቅት ከተነሱት ጉዳዮች አንዱ የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ይዞታ ነበር።የአዉሮጳ ሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ማኑኤል ባሮሶ ዛሬ የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚንስትር ካነጋገሩ በሕዋላ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ዘላቂነት የሚኖረዉ ሠብአዊ መብት ሲከበር መሆኑን አስታዉቀዋል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ጋዜጣዊ መግለጫዉን ተከታትሎ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሂሩት መለሰ

No comments:

Post a Comment