Thursday 26 September 2013

ኬንያና እንግሊዛዊቷ አሸባሪ፤

ኬንያ፤ በመዲናዋ በናይሮቢ ዌስትጌት በተባለው ግዙፍ የገበያ ህንጻ ውስጥ ፣ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ በሶማልያው አሸባብየአሸባሪዎች ቡድን፤ ቢያንስ72 ሰዎች ከተገደሉ ወዲህ ፣የ 67 ቱ ሰለባዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል ። የ3 ቀን የኀዘን ጊዜም ታውጆ ተግባራዊ በመሆን

ላይ ሳለ፣የዩናይትድ እስቴትስ፤ የብሪታንያ፤ የአሥራኤልና የሌሎችም ጠበብት ከኬንያ የምርመራ ጠበብትጋር በመተባበር፤ አደጋው እንዴትሊሠነዘር እንደቻለ በማጣራት ላይ መሆናቸውታውቋል። 40 ሚሊዮን ኑዋሪዎች ባሏት ኬንያ የሙስሊሞች ቁጥር 10 ከመቶ ገደማ ሲሆን፣ ተገቢ ቁጥጥር በማይደረግበት ድንበር፤ ሠርገው የሚገቡ የአሸባብ ታጣቂዎች ከአንዳንድ ኬንያውያን የእምነት ተጋሪዎቻቸው ድጋፍ እንዳልተለያቸው ተነግሯል። አሸባብ ፤ ሶማሌዎችን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሃገራት ተወላጆችንም ማሰለፉ ይነገርለታል። ከእነዚህም አንዷ ሳምንታ የተባለችው እንግሊዛዊት መሆኗ ታውቋል። ይህች ሴትዮ እንዴት በሽብር ተግባር ለመሰማራት ተነሳሳች? የለንደኑን ዘጋቢአችንን ድል ነሣ ጌታነህን በስልክ ጠይቄው ነበር።
audio ለመስማት ሊንኩን ይቻኑት

No comments:

Post a Comment