Wednesday 4 September 2013

ልማት ምንድነው? እውን የወያኔ መንግሥት ልማታዊ ነው?

September 4, 2013

ታደሰ ብሩ

1.           መግቢያ

“ሰላም ምንድነው?” በሚል ርዕስ ለፃፍኩት መጣጥፍ ከደረሱኝ በርካታ አስተያየቶች ውስጥ “በነካ እጅህ ልማት ምን ማለት እንደሆነ ብትገልጽልን” የሚለው ጥያቄ ለዚህ ጽሁፍ ምክንያት ሆኗል።
ከአሰልቺ የወያኔ ካድሬዎች ክርክሮች አንዱ “ልማታችን፣ ልማታችን” መሆኑ የማውቀውና በራሴም ላይ ከተራ ማሰልቸት በላይ የመብት ጥሰቶች ያደረሰብኝ ጉዳይ ነው። ወያኔ በአገራችን ላይ ላሰፈነው አገዛዝ ተቀባይነት (ligitimacy) ዋነኛ መከራከሪያው “ለኢትዮጵያ ልማትን ያመጣሁ፤ አሁንም በማምጣት ላይ ያለሁ መንግሥት ነኝ። ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ለማልማት ከኔ የተሻለ የለም” የሚል ነው። በዚህ ክርክር ውስጥ (1) ከዚህ በፊት በአገሪቱ ውስጥ ልማት የሚባል ነበር አልነበረም፤ (2) እኔ ልማትን እያመጣሁ ነው፤ ሌላውን ቻሉት፤ እና (3)  ለወደፊቱም ከኔ የተሻለ ኢትዮጵያን ማልማት የሚችል የሌለ በመሆኑ ለኢትዮጵያ  ሲባል  እኔ  ለረዥም ጊዜ  በስልጣን መቆየት አለብኝ የሚል መልዕክት አለው።
በዚህ ጽሁፍ እነዚህን ሶስቱም መከራከራዎች ውሸት መሆናቸውን ለማስረዳት እሞክራለሁ። ከሁሉ አስቀድሞ  ግን “ልማት” በተሰኘው ጽንሰ ሀሳብ ላይ የጋራ ግንዛቤ  እንያዝ።

2.      የልማት ትርጉም

በዛሬቷ ኢትዮጵያ መብራት ሲቋረጥ፤ ውሀ ሲጠፋ፤ ጤፍ ሲወደድ፤ መንደሮች ሲፈርሱ፤ የመኪና አደጋ ሲበዛ፤ ገበሬዎች ሲፈናቀሉ ሰበቡ ልማት ነው። ማናቸውም ችግር “እድገት ያመጣው ነው፤ ቻሉት” እየተባለ ይታለፋል። ለረሀብ፣ ለጥማት፣ ለበሽታ እና  መሰል መጥፎ  ነገሮች ልማት ምክንያት ሆኖ  ሲቀርብ፤ “መብቴ ይከበርልኝ ብሎ መጠየቅ “በፀረ-ልማትነት” ሲያስከስስ “ለመሆኑ ልማት ምንድነው?” የሚል የጅል አልያም የልጅ የሚመስል ጥያቄ ለማንሳት እንገደዳለን።
በቀላሉ ከሚገኝ  የwikipidia የኢኮኖሚ ልማት (Economic Development) ትርጓሜ  ልነሳ።
… የኢኮኖሚ ልማት  … በሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት፣ በዋና ዋና መሠረተ ልማት አቅርቦቶች፣ በአካባቢው ገበያ በሚኖር ተወዳዳሪነት፣ በምቹ የተፈጥሮ አካባቢ (ኢንቫይሮመንት)፣ በማኅበራዊ መስተጋብር፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በትምህርት እና በመሳሰሉ ነገሮች እድገት ማምጣትን ያካትታል[1]
የኢኮኖሚ ልማት የአንድ ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊና ማኅበራዊ ደህንነት የሚሻሻልባቸው ሂደቶችና ፓሊሲዎችን ያካትታል[2]። ልማት በቁጥር የሚለካ (Quatitative) ብቻ ሳይሆን በቁጥሮች መለካት የሚቸግር (Qualitative) ገጽታ  አለው። እንዲያውም የልማት ዋነኛ ግብ በቁጥሮች ለመለካት አስቸጋሪ የሆነውን “ደስተኛ  ማኅበረሰብን” መፍጠር ነው።
ልማት የአብዛኛውን ሕዝብ የዛሬ ኑሮ እና/ወይም የነገ ተስፋው ላይ ተጨባጭ አዎንታዊ  ለውጥ መፍጠር ነው። ይህም በአመጋገባችን፣ በጤናችን፣ በአለባበሳችን፣ በምናገኘው ትምህርት መጠንና ጥራት፣ በሚሰማን የራስ መተማመን ስሜት፣ በምናገኘው ፍትሃዊ ዳኝነት፣ በማኅበረሰቡ ባለው የመግባባት መጠን፣ በሚሰማን የነፃነት ስሜት … ወዘተ መገለፅ አለበት። በመጨረሻም የልማት ዋነኛው ግብ የድሀውን ድህነት መቀነስ እንጂ ሀብታሙን ይበልጥ ሀብታም ማድረግ አይደለም።
አሁን ወደ ትልቁ ጥያቄ  እናምራ። የወያኔ መንግሥት ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያደርግ መንግሥት ነው ወይ?[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

No comments:

Post a Comment