Saturday 28 September 2013

አቶ ግርማ ሠይፉ እና የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ተይዘው ተለቀቁ

የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ የአመራር አባላት ዛሬ ለሦስት ሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው መለቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡ግርማ ሠይፉ - እንደራሴ


ከተያዙት መካከል አንዱ “እጃቸው ያለመያዝ መብት” ያላቸው እንደራሴ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ግርማ ሠይፉ እንደሆነም ታውቋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት ሌሎች የፓርቲው አመራር አባላት መካከል ሊቀመንበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ዋና ፀሐፊው አቶ አሥራት ጣሴ፣ የሥራ አመራር ኮሚቴው አባልና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ዳንኤል ተፈራና ምክትላቸው አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባላት አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ስዩም መንገሻ እና አቶ ሺመልስ ሃብቴ፣ የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን፤ እንደሁም ሰላሣ ሦስቱ እየተባሉ ከሚጠሩት ስብስብ መካከል የሆኑ ሌሎችም ፓርቲዎች መሪዎች እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
ግርማ ሠይፉ - እንደራሴ

ለአራት ሰዓታት ያህል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የቆዩት የፓርቲው መሪዎች የተለቀቁት በማስጠንቀቂያ ሲሆን ሌሎች የፓርቲው የአዲስ አበባ አባላት የሆኑና ፖስተር ሲበትኑ የነበሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ወጣቶችን በዋስ ለማስለቀቅ እየተጣደፉ እንደነበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment