Saturday 3 August 2013

ሰበር ዜና (መንግስት ኹከት በመፍጠር ተጠምዷል!)

August 3, 2013

ድምፃችን ይሰማ
ቅዳሜ ሐምሌ 26/2005
ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሰላሙን እንዲያስጠብቅ መልእክት ተላልፏል!
በብዙ የአገሪቱ አካባቢዎች መረጋጋት እንዳይሰፍን መንግስት እየሰራ ይገኛል፡፡ የሙስሊሙ ሰላማዊነት እንቅልፍ የነሳው መንግስት ሁኔታዎች ወደ አለመግባባት እና ግጭት እንዲያመሩ እየሰራ ነው፡፡ ከሁለት ቀናት በፌት የጀመረውን የአፈሳ ዘመቻ አሁንም የቀጠለበት ሲሆን በተለያዩ ቦታዎችም ግጭትና ኹከት በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ መንግስት ትናንት ጁምአ በፍልውሃ መስጂድ ሰላት ሲሰግዱ የነበሩ ሙስሊሞችን በማወክና በመደብደብ በርካቶችን አስሮ ወስዷል፡፡Ethiopian Musilms
በዛሬው እለትም እስሩና ድብደባው የቀጠለ ሲሆን በኦሮሚያ አርሲ ዞን ከፍተኛ ኹከት በመንግስት ተቀስቅሶ የአራት ሰዎች ሕይወት በፖሊስ ጥይት መቀጠፉ ተገልጧል፡፡ የመንግስት ታጣቂዎች ምራብ አርሲ ኮፈሌ ታች ገጠር ውስጥ በመግባት በሙስሊሞች ላይ በሰነዘሩት ጥቃት የአካባቢው ኅብረተሰብ ከፍተኛ ችግር ውስጥ የወደቁ ሲሆን በአካባቢው መንቀሳቀስም አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ አንደምንጮች ፖሊስ መስጊዶች ላይ ጭምር ጥቃት እየሰነዘረና ሰላማዊውን ሕዝብ በማወክ ተጠምዷል፡፡

ሙስሊሙ ኅብረተሰብ መንግስት ሊፈጥር እያሰበ ያለውን ኹከት በመገንዘብና ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ በማሰብ የመንግስትን ትንኮሳ ቸል እንዲልና በትእግስት እንዲያሳልፍ አስቸኳይ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡ የመንግስት ቀዳሚው ፍላጎት መጀመሪያ እንደታየውም ኹከትና ግጭት በመፍጠርና ጥፋት በማድረስ፣ ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ለመወንጀልና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ለመጠቀም በመሆኑና ይህም በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ በመሆኑ፤ መንግስት ኹከት ሲቀሰቅስ በቸልታና አይቶ በማሳለፍ በመንግስት ወጥመድ ላለመውደቅ ሁሉም ጥረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ ከምንም በላይ ሰላማዊነታችን ዋጋ የምንሰጠው መሆኑን ሁላችንም ከግንዛቤ በመክት ሰላማችንን ሊነጥቁ የሚመጡ ኃይሎን በሰላም ብቻ እነድንመልሳቸው አደራ እንላለን፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment