Friday 16 August 2013

መንግስት የኢትዬጲያን ሙስሊሞች ከክርስቲያን ወገኖቹ ጋር ለማፋጀት የቅስቀሳ ወረቀቶችን እየበተ ነው:;

 

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች እና በአንዳንድ የክልል ከተሞች ላይ መንግስት ህዝበ ሙስሊሙን ከክርስቲያኑ ጋር የሚያጋጩ በራሪ ወረቀቶችን መበተን መጀመሩን ምንጮች አስታወቁ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በኮካ፣በጦር ሃይሎች፣በአየር ጤና እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች ላይ አስቸኳይ መልዕክት ለህዝበ ክርስቲያኑ የሚል ወረቀት በየመንገዱ መበተኑ ታውቋል፡፡
ይህ መንግስት የበተነው ወረቀት እንዲህ ሲል ጥሪውንይጀምራል :-
” አስቸኳይ መልእክት ለሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ”
“ከድምፃችን ይሰማ” አባላት መካከል እጅግ ሚስጥራዊእና ድንገተኛ በሆነ አጋጣሚ የተገኘ ትኩስ መረጃ ሁሉም ሊያነበው የሚገባ እና share ሊያደርገው የሚገባ ፖለቲካዊ እስልምና ና ጅሀድ (ቅዱስ ጦርነት)ሊያካሂዱ እንደሆነ አምልጦ የወጣ መሆኑን መረጃ ደርሶናል፡፡ ስለዚህም ሁላችሁም ጥንቃቄ እንድታደርጉ እና በአንድነት ሆነን ሰላማዊ ከሆኑ እስልምና ተከታዮች እንዲሁም ከመንግሰት ጋር ሆነን ይህንን አክራሪ ጽንፈኛ ፖለቲካዊ እስልምና ከስሩ ማድረቅ እና እንቅስቃሴውን መግታት፡፡
ከላይ እንዳነበባችሁት በዚህ በተበተነው ወረቀት ላይ 53 የሚጠጉ ነጥቦችን የተጠቀሱ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ በኢትዬጲያ ውስጥ ህገ መንገስቱ በፈቀደለት መንገድ እየተጠቀማቸው ያሉ የዜግነት መብቶቹን በሙላ ድብቅ አጀንዳ ማሳኪያቸው ነው በማለት ህዝበ ክርስቲያኑን ለማስደንበር እና በሙስሊሙ ላይ ጦርነት እንዲከፍት ለማነሳሳት ተሞክሯል፡፤
በ 20 አመታት ውስጥ ኢትዬጲያን የሙስሊም ሃገር ሊየደርጓት እቅድ ይዘው እንቀወሳቀሱ ነው፡፡ ኢስላማዊ መንግስት ከመሰረቱ ቡሀላ ክርስትናን ከኢትዬጲያ ምድር ለመሰረዝ ዋነኛ አጀነዳቸው ነው በማለት በወረቀቱ ላይ መንግስትህዝበ ክርስቲያኑን ለጦርነት እንዲነሱ ቅስቀሳ አድርጓል፡፤
በዚህ አደገኛ መልዕክት በያዘው ወረቀት ላይ ህዝበ ክርስቲያኑ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ያነሳውን ህዝበ ሙስሊም በጠላትነት እንዲፈርጅና እርስ በእስርስ እልቂት በመላው ሃገሪቱ እንዲፈጠር በማሰብ መንግስት ይህን አደገኛ ወረቀት እየበተነ እየበተነ ይገኛል፡፡
ለረጅም አመታት ተከባብሮ እና ለዋዶ በሰላም ሲኖር የነበረውን ህዝብ ለርካሽ የፖለቲካ ጥቅም ሲል መንግስት ለማፋጀት እና የእርስ በእርስ ጦርነት ለመቀስቀስ ከፍተኛ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
በህዝበ ሙስሊሙ ላይ መንግስት የጀመረውን ፀረ ህገ መንግስት የሆነ ሃይል እርምጃ ለመሸፋፈን በአክራሪነት እና በአሸባሪነት ላይ እንደሆነ ለማሰመሰል እና ክርስቲያን ወገኖችን ከጎኑ ለማሰለፍ የዚህ መሰሉን ለእርስ በእርስ ጦርነት የሚጋብዝ ወረቀት በየቦታው እየነበተ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ህዝበ ሙስሊሙ በተቀናጀ መልኩ መንግስት ባሁኑ ሰአት የጀመረውን መጠነ ሰፊ ህዝብን የማውደምዘመቻ ሁላችን በጋራ በመሆን ለህዝበ ክርስቲያኑ ቀድመን በማሳወቅ የበኩላችንን ሃላፊነት መወጣት|ይኖርብናል፡፤
ሃላፊነት በጎደላቸው የሃገሪቱ ባለስልጣናት እየተደረገ ያለው ህዝበ ሙስሊሙን ከክርስቲያን ወገኖቹ ጋር የማጋጨት እንቅስቃሴ በአላህ ፈቃድ ይከሽፋል፡፡
መንግስት የበተነውን ፀረ ህዝብ ቅስቀሳ ወረቀት አስፈላጊ ከሆነ ሙሉውን ፅሁፍ በድጋሚ ፖስት ይደረጋል፡፤
ሰላም እና ፍቅር ለኢትዬጲ ህዝቦች ይሁን!!!”"

No comments:

Post a Comment