Thursday 7 May 2015

እየከፋ የመጣው የወያኔ አፈና በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለምን?

                
ከ አብነት ዋሚ
May 07/2015
ከ ኖርዌይ በርገን
        ወያኔ ስፈር ቁጥር የሌለው በደል እና ግፍ ካደረሰባቸው ህዝቦች የ ኦሮሞ ህዝብ አንደኝው እና ዋነኝው ነው᎓᎓ ይህንን ስል የሌላው ብሄር ምንም አይነት በደል አልደረሰበትም ለማለት አይደለም᎓ በንጽጽር ግን የ ኦሮሞ  የከፋ ነው᎓ ሁል ጊዜ አንድ ጥያቄ በአምሮዬ ያጭርብኝል᎓ ይህን ሁሉ በደል እና ግፍ ከሌላው ብሄር በበለጠ ሁኔታ የኦሮሞ ህዝብ ላይ ለምን ይደርሳል᎓ በነገራችን ላይ ይህ ጥያቄ የእኔ ብቻ ጥያቄ  አይደለም የመላው የ ኦሮሞ ህዝብ ጭምር ነው ብዬ አምናለሁ   ታድያ ይህ ጥያቄ በእኔ ደረጃ ይመለሳል ብዬ ባላምንም እንደማንኝውም ጉዳቱ የተሰማው ኦሮሞ ያለኝን መላምት ለማስቀመጥ እሞክራለሁ᎓᎓ ወያኔ የ ኦሮሞ ህዝብን ከሌላው ብሄር በበለጠ  ማፈን ማሰር መግደል ማደህየት ማሰደድ የተቀረውን ደግሞ ፈሪ አድርጎ የ እራሱ ታዛዥ ማድረግ ዋናው አላማው ነው᎓᎓
        የ ኦሮሞ ህዝብን ማደህየት ስንል እንደሚታወቀው  የ ኦሮሚያ ክልል የቆዳ ስፍቱ እና በተፈጥሮ ሃብቱ በጣም ሃብታም ነው ታድያ ይህ ህዝብ በአብዛኛው አርሶአደር እንደመሆኑ መጠን ለዘመናት የኢትዮጲያን ህዝብ ሲመግብ የኖረ ህዝብ ነው᎓᎓ ታድያ በዘመነ ወያኔ ይህ ህዝብ እንዴት  እና ለምን ደህየ᎓ እንዴት ለሚለው ጥያቄ ወያኔ በገበሬው ላይ የማዳበሪያ እዳ በመቆለል በችግር እንዲማቅቁ በማድረግ፣ በጣም የተመረጡ እና ለም መሬቶችን በራሱ በህወሀት ካድሬዎች  በ INVESTMENT ስም በመቀማት፣ ሰፋፊ ምሬቶችን ለውጭ ባለሃብቶች በጣም በእርካሽ በመቸብቸብ ገበሬውን ከሚያርሰው መሬቱ ያለተመጣጣኝ ካሳ በማፈናቀል፣  በከተማ ማስፋፊያ ስም ለዘመናት ሲያርሱት ከነበሩበት መሬት ያለ ተመጣጣኝ ካሳ እና ምንም አይነት ምትክ ቦታ ሳይዘጋጅ ወይም ሳይሰጥ በማፈናቀል ሜዳ ላይ በመበተን፣ በከተሞች አካባቢ ያሉ የኦሮሞ ባለሃብቶችን ከ OLF ጋር ግንኝነት አላቹ በማለት ማሰር፣ ማንገላታት፣ እንዲማረሩ በማድረግ በመጨረሻም አደህይቶ እንዲሰደድ ማድረግ እና በተለያዩ የችግር አረንቋ ተብትቦ መብቱን እረስቶ ስለ እለት ጉርስ ብቻ እንዲያሰቡ በማድረግ ነው᎓᎓

        ከላይ እንደጠቀስኩት ወያኔ የኦሮሞ ህዝብን ለማፈን ብዙ ዘዴዎችን ይጠቀማል᎓ እንደሚታወቀው የ ኦሮሞ ህዝብ ከህዝብ ብዛቱና ከቆዳ ስፋቱ አንጻር በጣም ሰፊ እና በጣም ብዙ ህዝብ ነው᎓᎓ እናም ወያኔ ይህንን ህዝብ ለማፈን የተለያየ ዘዴዎችን ይጠቀማል አንደኛው እና ዋነኛው ከእሱ ሚዲያ ውጭ ሌላ ሚዲያ እንዳይሰማ እንዳያይ ማፈን እና በራሱ ሚዲያዎች የሃሰት ፕሮፖጋንዳውን በመንዛት ህዝቡን ማደንቆር ነው፣ ምንም አይነት በኦሮምኛ የሚታተም የኦሮሞ ህዝብ በራሱ ቋዋንቋዋ  በሳምንት ወይም  በወር አንድ ግዜ እንኩዋ የሚወጣ እና የሚያነበው ነጻ ጋዜጣ እንዳይኖር በማድረግ፣  ከሃገር ውጪ የሚተላለፉ የኦሮሞ ሚዲያዎችን ጃም እያደረገ ለህዝብ እንዳይደርስ በማድረግ፣ የተለያየ የ ኦሮሞ ድህረገጽዎችን በመዝጋት፣ የተለያዩ የ EMAIL እና የ FACBOOK  መልእክቶችን በመሰለል ያሰጉኛል ያላቸውን ሰዎች ስልክ በመጥለፍ የእራሱን ካድሬዎች በመጠቀም ታዋቂ የኦሮሞ ሰዎችን በመሰለል እና እኔ ባልጠቀስኩዋቸው የተለያየ የማፈኛ ዘዴዎችን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ይጠቀማል᎓᎓ ከእነዚ ሁሉ የ ወያኔ የማፈኛ ተንኮሎች አልበገር ያለውን ደግሞ በማሰር በማሰቃየት እና በመግደል ለማፈን  ይሞክራል᎓᎓ የተለያዩ የሰባአዊ መብት ድርጅቶች ባወጡት ሪፖርት መሰረት ከ ኢትዮጲያ እስር ቤቶች ውስጥ አብዛኛውን የሞሉት የኦሮሞ ልጆች መሆናቸውን ገልጸዋል᎓᎓ ወያኔ ከሌላው ብሄር በተለየ ሁኔታ ለምን የኦሮሞን ህዝብን ማሰር ማሰቃየት መግደል እና ማደህየት ፈለገ ብዬ ሳስብ ስልጣኑን ለማራዘም ወደሚለው  መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ ይመስለኛል ምክንያቱም የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ክልል ሲነጻጸር ከቆዳ ስፍቱ፣ ከህዝብ ብዛቱ እና በResource በጣም ሃብታም ነው᎓᎓ እና አሁን ያለውን የጭቆና ፖለቲካ የመቀልበስ ትልቅ አቅም ያለው ህዝብ ነው ወያኔ ታድያ ይህንን ትልቅ አቅም ያለው ህዝብን በማሰር በማሰቃየት እንዲራብ እንዲደህይ እንዲሰደድ በማድረግ አዳክሞ የስልጣን ግዜውን ለማራዘም ነው᎓᎓ የሰው ልጅ ከተራበ  እና ከተቸገረ አብዛኛውን ግዜ የሚያስበው እንዴት ምግቤን አግኝቼ የልጆቼን እና የራሴን ሂወት ላቆያት የሚለው እንጂ ሌላ የመብት ጥያቄዎችን ለጊዜውም ቢሆን ያዘገየዋል ታድያ የወያኔ ዋናው አላማው የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ይህንን ሰፊ ህዝብ ሀሳቡን በተለያየ ግፍ እና በደል ትኩረቱን ለማስቀየር ይሞክራል ይህንን ሰፊ ህዝብ በዚህ አይነት ካላዳከመ የስልጣን ጊዜው እንደሚያበቃ ያውቀዋል እና ገበሬውን እና ባለሃብቱን በእንደዚህ መልኩ ከተቆጣጠረ በሁዋላ የተማረውን እና ወጣቱን ደግሞ ከ OLF ጋር ግንኙነት አላቹሁ አሸባሪ ናቹ በሚል በማሰር በማሰቃየት በመግደል በማስፈራራት እና ከሃገር በማሰደድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ይፍጨረጨራል᎓᎓ አንድ ነገር ግን አስታውሱ ይህ ሁሉ የተቀናጀ አፈና ፣በደል እና ግፍ የኦሮሞን ህዝብ የነጻነት ትግል ቢያዘገየውም ሊያቆመው ግን በፍጽም አይችልም አልቻለምም እንደውም ከመቼውም በላይ የኦሮሞ ህዝብ ትግል  ተፏፉሞል᎓᎓    

No comments:

Post a Comment