Thursday 12 February 2015

ከዚህ በላይ ዉርደት የለም


ሁሉም የእግዛቤሔር ፍጥረቶች ሰዉ እና እንሰሳት ጭምሮ ምንም እንኳን ዓይነት እና ደረጃዉ የተለያየ ቢሆንም መብት አላቸው ።
በ 21 ክፍለ ዘመን አደጉ እና ሰለጠኑ የምንላቸው የዓለማችን ሀገሮች የእንሰሳት መብት ከሰው ልጅ መብት ባልተናነሰ ሁኔታ የሚከበርበት ደረጃ ላይ ተደርሶል። የነሱን መብት መጠበቅም ልክ እንደ አንድ የእድገት ደረጃ መቆጠር ከጀመረ ውሎ አድሮል። እነሱም ልክ እንደ አንደ ሰው ፍላጎት እና ስሜት አሏቸው ለምሳሌ ያህልም የህመም፣የደስታ፣የፍራቻ፣የብቸኝነት፣የስቃይ እና የእናት ፍቅር የመሳሰሉት ናችው። ለዚህም ነው ፍላጎታቸውን እና ስሜታቸውን የሚቃረን ተግባር መፈፀም የለበትም የሚሉ አያሌ የእንሰሳት መብት ተሞጋቾች የሚቃወሙት እና የሚታገሉት። መሀተመ ጋንዲ በአንድ ወቅት ¨የአንድ ሕዝብ ታላቅነት የሚለካው ወይም የምመዘነው ወይም የሚዳኝው ለእንሰሳት በሚሰጡት እንክብካቤ ነው ያሉት¨።
ዛሬ ግን ምስኪኑን ለፍቶ አደር የኦሮሞ ገበሬ ለነፃነት፣እኩልነት እና ፍትህ ብሎ የሚታገለውን እና ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት አልገዛም ያለውን ሰባዊ ከሆነ የፍጡር ደረጃ አወረዱት። ዛሬ ዓለም ለእንሰሳት ከምትሰጠው ክብር በታች አውርደውት ልክ እንዳልባሌ ነገር ቆጠሩት። ሰውን የሚያክል ክቡር ፍጡርን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በኃላ መሬት ለመሬት እየጎተቱ በአደባባይ መስቀላቸው ያቺ ሀገር መንግስት አልባ የተደራጁ የሽፍቶች ቡድን የምትገዛ መሆኖን ማሳያ ነው።
እነሱ ብቻ በተቆጣጠሩት የመገናኛ ብዙሀን የራሳቸውን የሽፍታነት ተግባር ለነጻነት ታጋዩ ምስኪን ገበሬ ይለጥፉለታል። አሽባሪ፣ጠባብ፣ሽፍታ፣ገንጣይ፣አስገንጣይ፣ጎጠኞ ወዘተ ይሉታል። ደርግም አኮ ፀረ ህዝብ ፣ፀረ አብዮት አያለ ነበር እኮ ሕዝብ ሲፈጅ የነበረው። እነዚህም በተመሳሳዩ የተለያየ ታርጋ እየለጠፉ ሕዝቡን ጨረሱት ::ታድያ እንዲት አንድ ጭብጥ ነቀዝ ወያኔ ማስወገድ አቅቶን እንዲህ ዓይነት ጭካኔ የተሞላበት ኢ-ሰባዊ የሆነ ድርጊት እና የሥም ማጥፋት ዘመቻ በሕዝባችን ላይ እስከ መቼ ሲፈፅመ ይኖራሉ? ነቀዝ ያልኩት ለመሳደብ ፈልጊም አይደለም ስድብ የኦሮሞ ባህልም አይደለምና። ቃሉን የተጠቀምኩት የወያኔን እና የነቀዝን ተመሳሳይነት እና አንድነት ለማሳየት ነው።
ሁለቱም ውስጥ ውስጡን እየበሉ ባዶ የሚያስቀሩ ተዋስያን ስለሆኑ ነው። በመሀከላችን የገቡትን እነዚን ተዋሲያን በመረባረብ ለአንዲ እና ለመጨረሻ ግዚ ማስወገድ ካልቻልን በታሪክ ተወቃሽ ከመሆን አናመልጥም ሌላም አካል ሊያስወግድልን አይመጣም። ¨surre jilbaa irraan dhumtee abbaatu warranata degaa Ijjollummaan dhuftee abbaatu tattafata¨ ይባላል።
ተማሪውን፣ገበሬወውን፣ሰራተኛውን፣ ከሕፃን አዋቂ ገደሉ፣አሰሩ፣አፈናቀሉ፣አሰደዱ፣የምንመካበትን የተፈጥሮ ሀብት መዘብሩ፣ትላልቅ መሬቶቻችን ወሰዱ፣ ወንዞቻችንን መረዙ። ከዚህም አልፈዉ የምስኪኑን ገብሬ ሬሣ በራሱ ቀያ ላይ በወገኖቹ ፊት መሬት ለመሬት ጎተቱ እጅ እና እግሩን ጠፍንገዉ ሰቀሉ ከዚህ በላይ ለኦሮሞ ሕዝብ ሞት ምን አለ? ከዚህ በላይ ወርደት ከወዲት ይመጣል?
የኦሮሞ ሕዝብ በዚያች ሀገር ላይ በብዛት ግንባር ቀደም ነው። ሕዝብ ደግሞ በየትያውም ዘርፍ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት አካል ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ሁለንተናዊ እድገት እና ነፃነት የማይታሰብ ነው። በተለያየ ግዜም ሕዝብ አምባገነን መንግስት ትብየው አካል ጋር እንዳሆነ አሳይቶል ወያኔም ሕዝብ አልባ አንደሆነ ይታወቃል። እየደረሰብን ካለው ውርደት ለመዉጣት አና ነፃነታችን ለመጎናፀፍ እያንዳንዳችን ባለን አቅም እና ችሎታ የምናበረክተው አስተዋፆ ለትግሉ አንድ ደረጃ መድረስ ለነፃነታችን ህውን መሆን ወሳኝነት አለው። ይህ በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ድርጊት የመታገል የሁላችንም ግዴታ ነዉ።
ድል ለኦሮሞ ሕዝብ
ከከልለው ኡር
ጋhttp://ayyaantuu.com/horn-of-africa-news/oromia/የወያኔ-ሴራ-ከነፃነት-ትግሉ-አያግደንም-ከ/

No comments:

Post a Comment