Tuesday 9 December 2014

የሳዑዲ ግብረ-ሠናይ ድርጅት ሆስፒታል በኢትዮጵያ

ድርጅቱ ቀደም ሲል ሆስፒታሉን አዲስ አበባ ዉስጥ ለመገንባት ጥያቄ ቢያቀርብም የከተማይቱ መስተዳድር ለሆስፒታሉ ማስገንቢያ የሚሆን መሬት ባለመፍቀዱ ትግራይ ዉስጥ ለማስገንባት ወስኗል።

አል ባስር የተሠኘ የሳዑዲ አረቢያ ግብረ-ሠናይ ድርጅት ሽሬ እንደ ስላሴ-ትግራይ ዉስጥ የዓይን ሕክምና መስጪያ ሆስፒታልና የሕክምና ባለሙያዎች ማሠልጠኛ ማዕከል ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አኖረ። ድርጅቱ ቀደም ሲል ሆስፒታሉን አዲስ አበባ ዉስጥ ለመገንባት ጥያቄ ቢያቀርብም የከተማይቱ መስተዳድር ለሆስፒታሉ ማስገንቢያ የሚሆን መሬት ባለመፍቀዱ ትግራይ ዉስጥ ለማስገንባት ወስኗል። ድርጅቱ ከትግራይ በተጨማሪ በኒ ሻንጉል፤ ሶማሊያ፤ ድሬዳዋና አፋር መስተዳድር ተመሳሳይ ሆስፒታሎች ለመገንባት አቅዷል።
http://www.dw.de/የሳዑዲ-ግብረ-ሠናይ-ድርጅት-ሆስፒታል-በኢትዮጵያ/a-18119004

No comments:

Post a Comment