Thursday 1 May 2014

በኦሮሚያ ግጭቶች ሕይወት ጠፋ

በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን በዋና ከተማይቱ ማስተር ፕላን ውስጥ አካትቶ ለማልማት በሚል የተያዘውን ዕቅድ ከተቃወሙ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በተነሣ ግጭት በሰው ይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የመንግሥት ኮመዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡


ፅ/ቤቱ ሐሙስ፣ ሚያዝያ 23/2006 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በመዳ ወላቡ የሦስት ተማሪዎች፣ በአምቦና ቶኬኩታዮ ከተሞች የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በቢዝነስና ኮንስትራሽን ባንክ ላይ የዘረፋ ሙከራ መደረጉን ገልጿል፡፡

በሃረማያ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች በተወረወረ ፈንጂ የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉንና ሌሎች ሰባ ተማሪዎች መቁሰላቸውን ፅ/ቤቱ በዚሁ መግለጫው አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በአምቦና አካባቢዋ “ቁጥራቸው 17 የሚደርስ ሰዎች ተገድለዋል” ሲል የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ - ኦፌኮ ከስሷል፡፡
ኦፌኮ የአካባቢውን ምንጮች ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ “የኢሕአዴግ መንግሥት ለዚህ የኃይል እርምጃ ተጠያቂ ነው” ብሏል፡፡

መግለጫው አክሎም “የኦሮሞና የአማራ ብሔረሰቦችን ለማጋጨትም ደባ እየተካሄደ ነው” ብሏል፡፡

http://amharic.voanews.com/

No comments:

Post a Comment