Wednesday 2 October 2013

ሊብያ ውስጥ የታሠሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ስደተኞች ብሦት

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች 

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር
  • ሊብያ ውስጥ የሚገኙ ከአምስት መቶ ሃምሣ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ስደተኞች ሰሃራ በረሃ ውስጥ በሚገኝ እሥር ቤት መታጎራቸውንና እንግልት እንደሚደርስባቸው በመግለፅ አማርረዋል፡፡

ስደተኞቹ በሊብያ ወታደሮች ከባድ ድብደባ ሲፈፀምባቸው መቆየቱን፣ ሴቶቹመ እንደሚደፈሩ ተናግረዋል፡፡

ስደተኞቸ በተጨማሪም በቂ ምግብ፣ ውኃ፣ የፅዳትና የንፅሕና እንዲሁም የጤና አገልግሎት እንደማያገኙ፣ የሚኖሩትም በሰሃራ በረሃ ውስጥ በተጨናነቀ ክፍል ውስጥ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር የሊብያ ተጠሪ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ስደተኞቹ በሊብያ መንግሥት ውሣኔ ወደ እሥር ቤቱ እንዲጓጓዙ መደረጉን ገልፀው እርሣቸው ግን እንደ ስደተኞች መሥሪያ ቤት ከእሥር ቤት እንዲወጡና ወደ ትሪፖሊ እንዲሄዱ ለማድረግ እየጣሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

http://amharic.voanews.com/

No comments:

Post a Comment