Thursday, 18 April 2013

የኢትዮጵያና የአዉሮጳ ሕብረት መሪዎች ዉይይት


የአዉሮጳ ሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ማኑኤል ባሮሶ ዛሬ የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚንስትር ካነጋገሩ በሕዋላ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ዘላቂነት የሚኖረዉ ሠብአዊ መብት ሲከበር መሆኑን አስታዉቀዋል

አዉሮጳን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ዛሬ ብራስልስ-ቤልጅግ ዉስጥ ከአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት ከማኑኤል ባሮሶ ጋር ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩን ትናንት ሽትራስ ቡርግ-ፈረንሳይ ዉስጥ ያነጋገሩት የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ማርቲን ሹልስ ዛሬ እንዳስታወቁት በትናንቱ ዉይይት ወቅት ከተነሱት ጉዳዮች አንዱ የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ይዞታ ነበር።የአዉሮጳ ሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ማኑኤል ባሮሶ ዛሬ የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚንስትር ካነጋገሩ በሕዋላ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ዘላቂነት የሚኖረዉ ሠብአዊ መብት ሲከበር መሆኑን አስታዉቀዋል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ጋዜጣዊ መግለጫዉን ተከታትሎ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሂሩት መለሰ

ከፍንጂ ማምከኛ ድርጅት በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ሀብት ተዘረፈ


ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአፍሪካ ውስጥ ካሉ ሶስት የፈንጅ አምካኝ ድርጅቶች መካከል በአገልግሎት ዘመኑም ሆነ በተግባሩ በግንባር ቀደምነት ስሙ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ፈንጅ አምካኝ ድርጅት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እንደፈርስ መደረጉን ተከትሎ፣ ከተለያዩ የውጭ አገራት በእርዳታ ከተሰጠው በመቶ ሚሊዮኖች ከሚቆጠር ገንዘብ በተጨማሪ፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቹ በወታደራዊ መኮንኖች እንዲዘረፍ መደረጉን የውስጥ ምንጮች ገለጹ።
አብዛኞቹ የድርጅቱ ከባድ መኪናዎች እና ሌሎች ንብረቶች በወታደራዊ አዛዦች መወሰዳቸውን የገለጡት ምንጮች ጉዳዩ ያሳሳበው የጸረ ሙስና ኮሚሽን ምርመራ ቢጀምርም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ምርመራውን አቋርጣል።
ከ100 እስከ 150 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ መዘረፉን የገለጡት ምንጮች፣ ከዝርፊያው ጋር እጃቸው አለበት የተባሉት መኮንኖች በዘረፉት ገንዘብ ከፍተኛ ህንጻዎችን እያስገነቡበት መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአንድ የመምሪያ ሀላፊነት ቦታ ላይ የነበሩ ሰው ድርጅቱ  ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገለት በጥሩ ሁኔታ ሲሰራ ከቆየ በሁዋላ፣ በድንገት የተወሰኑ ወታደራዊ አዛዦች በድንገት ተመካክረውና በቂ ጥናት ሳይደረግበት ከ7 መቶ በላይ ሰራተኞችን በማባረር እንዲፈርስ አድርገውታል ብለዋል። ወታደራዊ አዛዦቹ የተወሰኑ ቁሳቁሶችን ለፌደራል ፖሊስ ያስረከቡ ቢሆንም፣ አብዛኛውን ንብረት ያለጠያቂ በመከፋፈል መውሰዳቸውን እኝሁ ባለስልጣን ገልጸዋል።

ኢህአዴግን በጓሮ ድርድር የጠየቀበት ሰነድ ተተረጎመ!


“የመሬት ነጠቃ” ዜጎችንና የተፈጥሮ ሃብት እየበላ ነው

cover 6


በልማትና ኢንቨስትመንት ስም ኢህአዴግ ለውጪና ለራሱ ሰዎች እየቸበቸበ ያለውን መሬት አስመልክቶ የኦክላንድ ተቋምና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በጋራ ያዘጋጁት ጥናታዊ ዘገባ አማርኛ ትርጉም በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ ይደረጋል ተባለ። የመሬት ነጠቃ ዜጎችን እያፈናቀለና ውድ የተፈጥሮ ሃብትን እየበላ ነው።
እመራቸዋለሁ ለሚለው ህዝብና አገር ደንታ የሌለው ኢህአዴግ፣ በመረጃ ለሚያጭበረብራቸው ዜጎች የተሟላና የተመጣጠነ ዘገባ እንደሚያቀርብ የተነገረለት ይህ ሰነድ በአማርኛ ተተርጉሞ ይፋ እንደሚሆን የገለጸው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ዴስክ ነው።
የጋራ ንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ዴስክ በተለይ ለጎልጉል በሰጠው መረጃ በጥናቱ ሰለባዎች፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ኢንቨስተሮች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች፣ የቅርብ ምስክሮች፣ የተለያዩ ከዓለምአቀፍ ተቋማት የተገኙ መረጃዎች፣ መንግስት ራሱ ይፋ ያደረጋቸው መረጃዎችና ለጥናቱ አስፈላጊ የተባሉ አኻዞች ተካተውበታል።
በዚሁ መሰረት ኢህአዴግ በልማትና በኢንቨስትመንት ስም “ጥቅም ላይ ያልዋለ መሬት” በማለት ለንግድ ማቅረቡና፣ ይህም በመደረጉ አገሪቱ ውስጥ ልማት እንደሚስፋፋ የሚሰብከው ስብከት ያለ አንዳች ማስተባበያ እርቃኑን የሚያስቀረው ሪፖርት በዋናነት የተዘጋጀው መረጃ ለጠማው ህዝብ እንደሆነ ዴስኩ አስታውቋል።
አገራቸውን፣ መሬታቸውንና መንግስትን አምነው የሚኖሩ ዜጎችን በገንዘብ በመለወጥ ያፈናቀለውና እያፈናቀለ ያለው ኢህአዴግ፣ ምትክ የሌላቸውን እድሜ ጠገብ የተፈጥሮ ደኖች ጨፍጭፏል፤ አቃጥሏል፤ አውድሟል። ሰፊ መሬት ምድረ በዳ አድርጓል። ያለ አንዳች ምክርና ውይይት ዜጎችን አፈናቅሎ ለመከራ ዳርጓል። ንብረታቸውንና ማሳቸውን እንደ ባዕድ በዶዘር ጠርጎባቸዋል። ለመቃወም በሞከሩ ወገኖች ላይ የባዕድ ወራሪ ሃይል ይፈጽመዋል ተብሎ የማይገመት ወንጀልና መከራ አድርሷል። የጋራ ንቅናቄው የሚዲያ ዴስክ እንዳለው ኢህአዴግ ይህንን ሁሉ ሲፈጽም ጎን ለጎን ዜጎችን በመረጃ እያጭበረበረና እያስራበ በመሆኑ አሁን ይፋ የሚደረገው ሪፖርት ታላቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

“ትግራይን” የመመስረት የ 21 ዓመታት ጉዞ


ዕውነቱ ታየ(ከባህር ዳር)

ዕውነቱ ታየ (ከባህር ዳር)
በ1968 ዓ ም ባወጣው ማንፌስቶ ህወሓት “ታላቋን ትግራይ” ከኢትዮጵያ ገንጥሎ የራሷን ሪፐብሊክ እንድትመሠረት የማድረግ ግብ ነድፎ እንደነበር የግንባሩ መስራች አባላትThe 1976 TPLF Manifesto TPLF’s “Republic of Greater Tigray” የመሰከሩት ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያዊነቱ በሚኮራው የትግራይ ሕዝብ ማንፌስቶው ተቀባይነት እንደማያገኝ የሕወሓት መሪዎች ሲረዱ ትተነዋል ብለው ቢያውጁም እነመለስና ስብሀት ግን ለ 21 ዓመታት ሲፈፅሙት የኖሩት ያን ግብ ለማሳካት ነበር። ዋና ዋናወቹን ክንውኖች እንመልከት፦
1ኛ. ህወሓት ጫካ እያለ የሰራውን “የታላቋን ትግራይ” ካርታ እውን ለማድረግ ከጎንደርና ከወሎ ሰፋፊ ለም መሬቶችን በማንአለብኝነት በመውሰድ ወደትግራይ ከለለ። ኢትዮጵያን በዘር ሸነሸነ፤ ኢትዮጵያዊያንን በዘር በመከፋፈል ስለ አንድነታቸው ሳይሆን ስለልዩነታቸው እያሰቡ እንዳይተባበሩ ለማድረግ ተጣጣረ፤ በኢትዮጵያዊነት ላይም ዘመተ።
2ኛ. ሕወሓት ባረቀቀው አዲስ ህገ መንግስት “የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል ድረስ” የሚል አንቀፅ አስገባ፤ በአንቀፅ 39 ላይ ተቃውሞ ሲነሳ መለስ ንዴቱን መቆጣጠር ተስኖት በቁጣ መልስ ይሰጥ እንደነበር እናስታውሳለን።

Tuesday, 16 April 2013

April 16, 2013 RAB kabajaa GGO Oslo fi Wellington


Ethiopian journalist Reeyot Alemu wins 2013 UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize


Imprisoned Ethiopian journalist Reeyot Alemu has won the 2013 UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize.

Reeyot Alemu, the 31 year-old young Ethiopian heroine of press freedom
Reeyot was recommended by an independent international jury of media professionals in recognition of her “exceptional courage, resistance and commitment to freedom of expression,” UNESCO said in a press release on Tuesday. The Jury took note of Reeyot Alemu’s contribution to numerous and independent publications. She wrote critically about political and social issues, focusing on the root causes of poverty, and gender equality. She worked for several independent media. In 2010 she founded her own publishing house and a monthly magazine called Change, both of which were subsequently closed. Alemu was arrested n June 2011, while working as a regular columnist for Feteh, a national weekly newspaper. She is currently serving a five year sentence in Kality prison.

Monday, 15 April 2013

Somalia: Telecom Growth Rate, in a Lawless Country, is Three Times Greater Than Ethiopia



Alcatel-Lucent contractors lay the TEAMS fibre optic cable on the Fujairah shore-end in the UAE
SomCable drags the EASSy Submarine cable from Djibouti to Somalia. The cable connects Somalia (Berbera, Mogadishu), Djibouti, Kenya to South Africa and Europe. It also has landing points in Sudan (port Sudan)
The use of Skype and Google talk are limited and tightly monitored in Ethiopia.
Ethio Telecom, formerly the Ethiopian Telecommunications Corporation (ETC) is the sole Government controlled telecom.
In contrast, Somalia offers some of the most technologically advanced and competitively priced telecommunications and internet services in the world.
Somalia telecoms offer many services that are not even available throughout the continent. Customers can conduct money transfers (such as through the popular Dahabshiil) and other banking activities via mobile phones, as well as easily gain wireless Internet access.There are over 20 telecom companies in Somalia and they offer the cheapest and clearest phone calls in Africa. There are presently around 25 mainlines per 1,000 persons, and the local availability of telephone lines (tele-density) is higher than in neighboring countries; three times greater than in adjacent Ethiopia.