Thursday, 10 July 2014

የአቶ አንዳርጋቸው ይዞታና የሂዩመንራይትስ ዋች ጥሪ

የመን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፋ የሰጠቻቸው የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በኢትዮጵያ እሥር ቤት ውስጥ ይበደላሉ ብሎ እንደሚፈራ ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ ።

Human Rights Watch Logo
የድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ ሚስ ሌስሊ ሌፍኮው ድርጅታቸዉ ሥለ ኢትዮጵያ የእስረኞች ይዞታ ያለዉን ልምድ ጠቅሰዉ እንዳሉት አቶ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ እሥር ቤት ይንገላታሉ የሚል ስጋት አለው ። ሌፍኮው የብሪታኒያ መንግሥት የአቶ አንዳርጋቸው መብት እንዲከበር አስፈላጊውን ጫና እንዲያደርግም ጠይቀዋል ።የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ኢትዮጵያ እስር ቤት ዉስጥ በደል-ይደርስባቸዋል ለማለት ሑዩማን ራይትስ ዋች የመጀመሪያዉ አይደለም።ሌላዉ አለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽንልም ባወጣዉ መግለጫ ተመሳሳይ ሥጋቱን አስታዉቋል።

Monday, 7 July 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውን ሂውማን ራይትስ ወች ገለጸ

ሰኔ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፎ መሰጠቱን ከታማኝ ምንጭ ማግኘቱን ገልጿል።

የየመን ባለስልጣናት ሰነዓ ከሚገኘው ኤል ራህባ አየር ማረፍያ ላይ እኤአ ጁን 23 ወይም 24 ከእንግሊዝ ኢምባሲ ጋር እንዳይገናኝ አድርገው አቶ አንዳርጋቸውን ወዲያውኑ ወደ ኢትዮጵያ ልከውታል ሲል ሂውማር ራይተስ ወች አስታውቋል።
የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው የአቶ አንዳርጋቸው ደህንነት እንደሚያሰጋቸው ገልጸው፣ መንግስት ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጠበቆቻቸውና ከእንግሊዝ ኮንሱላር ሰራተኞች ጋር እንዲገናኙ እንዲፈቅድ ጠይቀዋል።
አለም በሙሉ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ በአንክሮ እየተከታተለው መሆኑን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ልብ ሊሉት ይገባል ሲሉ ሌፍኮው ተናግረዋል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ ደግሞ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን በሃይል ወደ ኢትዮጵያ እንዲወሰዱ መደረጋሸውን  በአገሪቱ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን ጠቅሶ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እንደሚደርስባቸው የገለጠው አምነስቲ፣ በአቶ አንዳርጋቸውም ላይ ከፍተኛ ስቃይ ሊደርስበት ይችላል ሲል አክሏል።
አምነስቲ አያይዞም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከጎረቤት አገሮች የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር በርካታ ኢትዮጵያውያን ያለፍላጎታቸው ወደ አገራቸው እንዲመለሱና ስቃይ እንዲደርስባቸው እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።
አምነስቲ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው የታሰረበትን ቦታ እንዲያስታውቁ ጠይቋል።

የአቶ አንዳርጋቸዉ እገታና የመብት ተሟጋቹ ተቋም

የአዉሮጳ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመን-ርዕሠ ከተማ ሰነዓ አዉሮፕላን ማረፊያ ተይዘዉ ወደ ኢትዮጵያ ተግዘዋል የተባሉትን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌን ለማስፈታት እንዲጥሩGESELLSCHAFT FÜR BEDROHTE VÖLKER የተሰኘዉ የጀርመን የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠየቀ።

Flash-Galerie Airbus A 350 800 XWB
ለተጨቆኑ ሰዎች ጥብቅና የቆመዉ ድርጅት ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ አቶ እንዳርጋቸዉ ፅጌንም ሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያ ዉስጥ የታሠሩ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ለማስፈታት የአዉሮጳ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠብአዊ መብት ምክር ቤት ጣልቃ መግባት አለባቸዉ።
GESELLSCHAFT FÜR BEDROHTE VÖLKER ማለት የሚታወቀዉ በጀርመን ጎቲንገን ከተማ የሚገኘዉ ለተጨቆኑ ሰዎች ጥብቅና የቆመዉ ድርጅት የአዉሮጳዉኅብረት እና የተመ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ናቪ ፒላይ፤ የት እንደደረሱ እስካሁን በግልፅ ያልታወቀዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ መሪ የአቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ የት እንደሚገኙና፤ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እንዲያደርጉ ጠየቀ።«ለዲሞክራሲያዊትዋ ኢትዮጵያ የሚናገሩት የታዋቂዉ የተቃዋሚዎች መሪ የአቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ደህንነት እጅግ አሳስቦናል ሲሉ የድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ኃላፊ ኡልሪሽ ዲሉስ ዛሪ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቀዋል። በእዉነት በአሁኑ ወቅት አቶ እንዳርጋቸዉ ፅጌ የት እንደሚገኙ ድርጅታቸዉ የሚያዉቀዉ ነገር የለምን? 

Amnesty International: Ethiopian activist Andargachew Tsige at risk of torture

July 6, 2014

URGENT ACTION ETHIOPIAN ACTIVIST AT RISK OF TORTURE

Andargachew Tsige, an Ethiopian political activist in exile, appears to have been arrested in transit in Yemen on 24 June and forcibly returned to Ethiopia. He is at risk of torture and other ill-treatment. Andargachew Tsige is a British national of Ethiopian origin and Secretary-General of Ginbot 7, an outlawed Ethiopian opposition group. He disappeared on 24 June at Sana’a airport in Yemen, while in transit between the United Arab Emirates and Eritrea. Although no official statements have been released by the Yemeni or Ethiopian authorities about his current whereabouts, human rights activists in Yemen told Amnesty International that he was forcibly returned to Ethiopia the same day he landed after being detained at the Sana’a airport.Amnesty International on Andargachew Tsige
He is at high risk of torture and other ill-treatment in Ethiopia, where political detainees are frequently tortured in order to extract information and confessions. His incommunicado detention in an unknown location increases this risk.
Ginbot 7 is one of five organisations proscribed as terrorist organisations by the Ethiopian parliament in 2011. In 2012, Andargachew Tsige was prosecuted in absentia on terrorism charges (alongside journalist and prisoner of conscience Eskinder Nega, and others) and sentenced to life imprisonment. Previously, in 2009, he was convicted in absentia on charges related to an aborted coup attempt and was sentenced to death. He was also tried in absentia in the 2005-2007 trial of political opposition members, journalists, activists and others.

Saturday, 5 July 2014

አቶ አንዳርጋቸው “ለኢትዮጵያ መንግሥት ተሰጡ” ሲል ግንቦት ሰባት አስታወቀ

የየመን መንግሥት የግንቦት ሰባትን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ሰጥቷል ሲል ግንቦት ሰባት አስታውቋል፡፡
ግንቦት ሰባት በዌብ ሳይቱ ላይ ባሠፈረው መግለጫ “የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቶ መቆየቱ ማስታወቃችን ይታወሳል።” ብሏል፡፡
ግንቦት ሰባት ይቀጥልና “የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቄዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም - ይልና - የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል።” ብሏል፡፡ “በዚህም ሳቢያ - ይላል የግንቦት ሰባት መግለጫ - የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ፤ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወዳጅ ጎረቤት ትሁትና ቀና ቢሆንም ጥቃት በሚያደርስበት የቅርብም ሆነ የሩቅ ጎረቤት ላይ ግን ቁጣውን የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ያውቅበታል።”

አዜብ መስፍን በጠና ታመዋል፤ የአባዱላ ገመዳ ልጅ አረፈ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ ከፖለቲካው መድረክ እየተገለሉ የመጡት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በጠና መታመማቸውን ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። በስኳር ህመምና በደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት አዜብ መስፍን የሰውነት ክብደታቸው እንደቀነሰና የመጎሳቆል ሁኔታ በገጽታቸው እንደሚታይ የጠቆሙት ምንጮቹ ለስኳር በሽታ በየእለቱ ከሚወስዱት መድሃኒት በተጨማሪ ለደም ግፊትም እንክብሎችን እንደሚወስዱ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። አዜብ በመኖሪያቸው አብዛኛውን ቀናት እንደሚያሳልፉ የጠቆሙት ምንጮቹ በፖለቲካው የደረሰባቸው ኪሳራ ብስጭት ውስጥ እንደከተታቸውና ለበሽታ እንደዳረጋቸው አያይዘው ገለጸዋል።
ቦሌ ከሳይ ኬክ ቤት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኘውና አቶ ስዩም መስፍን ለ19ዓመት የኖሩበት እንዲሁም አቶ ሙክታር ከድር ለሁለት አመት የኖሩበት መኖሪያ ቪላ ውስጥ የሚኖሩት አዜብ መስፍን ከዚህ በተጨማሪ ቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ላይ የሚገኘውን የቀድሞ የደህንነት ቢሮ ለአዜብ በቢሮ መልክ እንደተሰጣቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል።
በዚህ ቢሮ ለብቻቸው ያሳልፉ የነበሩት አዜብ መስፍን በጠና ከታመሙ ወዲህ ላለፉት አምስት ሳምንታት ወደዚህ ቢሮ ገብተው እንደማያውቁና በቤታቸው እንደሚያሳልፉ ያስታወቁት ምንጮቹ አክለውም ፓርቲው በሚያካሂዳቸው ስብሰባዎች መገኘት እንዳቆሙና ለመጨረሻ ጊዜ የተገኙት ከሁለት ወር በፊት ኢህአዴግ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ላይ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚሁ ጉባኤ ከተሰብሳቢው ኋላ ለብቻቸው ተቀምጠው የታዩት አዜብ ምንም ሳይናገሩና አስተያየት ሳይሰጡ ስብሰባውን ከመጨረሳቸው ባሻገር ከስተውና ተጐሳቁለው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰው ከዚያ ወዲህ ህመሙ እየጠናባቸው እንደሄደ አያይዘው ገለፀዋል። አዜብ የባለቤታቸውን ቦታ በመተካት የጠ/ሚ/ርነቱንና ፓርቲውን የመምራት እቅድና ምኞት በተቀናቃኛቸው ስብሃት ነጋ ከከሸፈባቸውና የሚተማመኑባቸው የደህንነት ባለስልጣናትና የፓርቲው ቁልፍ ሰዎች እስር ቤት መወርወርና መባበረር ለከፍተኛ የሞራል ድቀትና ለበሽታ እንደዳረጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። አዜብ የኤፈርት ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ተብለው ቢሰየሙም ምንም አይነት የአመራር ሚና እንደሌላቸው የጠቆሙት ምንጮቹ በነስብሃት ተመድበው ተቋሙን ሲመሩ የቆዩት አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ወደ ራዲዮና ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ እንደሆኑና ከርሳቸው በኋላ ደግሞ የአርከበ እቁባይ ታናሽ ወንድም ጌታቸው እቁባይ እየመሩት መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል።

Sunday, 29 June 2014

ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ ”ሞት ሊበየንበት ይችላል” -በሽብርተኝነት ክስ ሞት ተፈርዶባቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁ 127 ሰዎች ኣሉ

በኖርዌይ ሃገር ውስጥ በኖርዌጂያንኛ የሚታተመው ዳግብላደት የተባለው ጋዜጣና ድረ-ገጽ ”ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን” ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ በሚቀጥለው ሳምንት ሞት ሊበየንበት ይችላል” ሲል ኣውጥቶኣል።

”ባለፈው ሳምንት ለማወቅ እንደተቻለው ዕድሜው 52  የሆነና  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ  የተባለ ኖርዌጂያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል።” tiltalt for terror በማለት የጀመረው የኖርዌዩ ዳግብላደት ሲቀጥልም…”የኢትዮጵያ መንግስት ቃለ ኣቀባይ እንደሚለው ገንዘብ ኣሰባስቦና ኣጥቂ ቡድን መልምሎ ኣደጋ ለማድረስ ሲሞክር ያዝነው በማለት መከሰሱን ያትትና በበኩላቸው የኖርዌዩ የሰብኣዊ መብት ጥበቃም ሆኑ የዓለም ኣቀፉ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን በጥብቅ ያወገዙት ሲሆን፣ ኣያይዘውም ለዚሁ ድረ-ገጽ ታሳሪው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ከወትሮው የከፋ እንደሆነም ስጋታቸውን እንደገለጹለት ያወሳል።
 ኢትዮጵያንም ሆነ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት፣ በኣሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ የሚገኙትን  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ ”በሚገባ ያውቃሉ” ያሉዋቸውን የሰብኣዊ መብት ተሟጋችና ኖርዌጂያን ፈሊክስ ሆርነ ን  ኣነጋግሮ ድረ-ገጹ ያገኘው መልስ ”ኖርዌጂያኑን ኦኬሎ በሚቀጥለው ሳምንት የሚሰየመው ችሎት ሞት ሊበይንበት ይችላል” በማለት የገለጹ ሲሆን ኣክለውም፣
”በሃገሪቷ ውስጥ በሽብር ወንጀል የሚከሰሱት ዜጎች የሚገጥማቸው የሞት ፍርድ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሞት የሚፈረድባቸው ዜጎች ምንም ማስረጃ ያልቀረበባቸው ናቸው። በሽብር ክስ ስለተከሰሱ ብቻ ዕድላቸው ይሄው ነው። በሞት ቀጠና የሚገኙትን ዜጎች የሚዘግበው ዓለም ኣቀፉ ድርጅት በኢትዮጵያ በእስር ቤት ውስጥ በሞት ቀጠና (ሴል) የሚሰቀሉበትን ወይም የሚገደሉበትን ጊዜ የሚጠባበቁ 127  ዜጎች  ይገኛሉ ሲል ፈሊክስ ሆርነ ለድረ- ገጹ ገልጸዋል።