Tuesday 31 March 2015

የአውሬው መንግስታችን አሳፋሪ ድርጊት በኦሮሞ ህዝብ ላይ

ከ አብነት ዋሚ
March 27/2015
Norway Bergen
      በዚህ ባሳለፍነው 24 አመት እውነት  ህዝባችንን የሚመሩት ሰወች ናቸው የሚለው ነገር ሁል ጊዜም እንድጠራጠረው የሚያደርገኝ ብዙ በደሎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሃገሪቶዋን እየመራ ባለው በTPLF ተፈጽሞል᎓᎓ እነዚህ ሁሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ግፎች በራሳቸው ህዝብ ላይ እየፈጽሙ እና እያስፈጸሙ  ያሉት አሸባሪዎች የሰው ፍጡር ናቸው የሚለውን ለመቀበል አእምሮዬ ባያምንበትም እነዚ ገዳዮች ሰው መሆናቸውን ከመቀበል ውጭ አማራጭ አልነበረኝም

       ባሳለፍነው አመት December 9/2014 ግን ከ እስከዛሬው ለየት ያለና እነዚ ጨካኞች ሰው አለመሆናቸውን ያረጋገጠልኝ ለሰሚው ሁሉ የሚዘገንን ግፍ በ ኦሮሞ ህዝብ ላይ ተፈጽሞዋል᎓᎓ በተለምዶ ብዙ የእግዚአብሄር ፍጡራን የሆኑ ምድባቸው ከዓውሬ የሆኑ እንስሳት እግዚአብሄር ከሰውልጅ ልዩ ባህሪ እንዲኖራቸው አድርጎ ነው የፈጠራቸው ከልዩነታቸው መሃከል እኔ መጥቀስ የፈለኩት ወይም ከጽሁፌ ታሪክ ጋር ይሄድ ዘንድ የአውሬነት ባህሪያቸውን እና አመጋገባቸውን ነው᎓᎓ አብዛኛውን ጊዜ አውሬዎች ምግባቸውን የሚያገኙት በአደን ነው የሚያድኑትንም እንስሳ ይዘው ከገደሉ ወይም እንዳያመልጥ አድርገው ካደቀቁት በሁዋላ ወደሚፈልጉበት ቦታ ወይም ተረጋግተው ለመመገብ የሚያመቻቸው ቦታ እስኪደርሱ ሬሳውን መሬት ለመሬት እየጎተቱ ይወስዱታል ታድያ አንድ ነገር ላስታውሳቹ እንደዚህ አይነት ባህሪ ያላቸው ፍጡራን ምድባቸው ከአውሬ ነው ስማቸውም አውሬ ይባላል᎓᎓ ይህንን እንደመንደርደሪያ ያነሳሁላቹ ስለፍጡራን ባህሪይ ልነግራቹህ ወይም ላስረዳቹ ብዬ ሳይሆን በቅርቡ በወያኔ ካድሬዎች የተፈጸመውን አሰቃቂ እና ኢሰብአዊ ድርጊት ነው በኦሮሚያ ውስጥ በደራ ወረዳ በጊንዳ ቀበሌ December 9/2014 ከተማ ውበቱ እና ጕደኛውን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በሁዋላ በከተማ አደባባይ ላይ መሬት ለመሬት እየጎተቱ በአደባባይ በህዝብ ፊት ሰቀሉዋቸው᎓᎓ አንድ በህገመንግስት ወይም በህግ ህዝቤን አስተዳድራለው ከሚል መንግስት እንደዚ አይነት የአሸባሪ ድርጊት ወይም ኢሰብአዊ (አውሬአዊ) ድርጊት የሚጠበቅ ነውን ጎበዝ ምን እየሆንን ነው ያለነው ምንስ እየጠበቅን ነው ያለነው የእኛ ውርደት እኮ ማብቂያ አጣ ሰው በህይወት እያለ ተዋርዶ ሲሞት እሬሳውን ለቤተሰብ ሰጥቶ በክብር እንዳያርፍ ማድረግ ምን ማለት ነው ኢሄ የሰው ባህሪ ነውን ሰዎች እንደዚህ አይነት ፍጽም ኢሰባአዊ የሆነ አረመኔአዊ ድርጊት የሚፈጸሙ TPLF እና የ TPLF ካድሬዎች ምድባቸው ከሰው ነው ትላላቹ እኔ ግን ከአውሬ መድቤያቸዋለው የእናንተን ለእናንተ ትቼዋለው᎓᎓
       እንደዚ አይነት አሰቃቂ እና ኢሰብአዊ ድርጊት የተፈጸመው መንግስት አልባ በሆነችው በሶማሊያ ነው᎓᎓ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 1993 በአሜሪካ ወታደሮች ላይ እና በ ቅርቡም በ አፍሪካ የሰላም አስከባሪ አገራት ወታደር በሚባሉት የኢትዮጲያ፣ዩጋንዳ፣ኬንያን ጨምሮ ነበር ታዲያ ይህንን አይነት ኢሰብአዊ ድርጊት የተፈጸመው ሶማሌያዊያን በውስጥ ጉዳያችን የማንንም ባአድ ሃገር ጣልቃ ገብነት በመቃወም የተቀሰቀሰ ቁጣ ነበር᎓᎓ ታድያ አሁንም የማስታውሳቹ ነገር ቢኖር እነዚህ ኢሰባአዊ ድርጊቶች ሲፈጸሙ ሶማሊያ በእርስበእርስ ጦርነት ላይ የነበረች እናም መንግስት አልባ የነበረች ሃገር ነበረች
       ከሶማሊያ በፊት እንደዚህ አይነት ጭካኔ የታየው ከዛሬ 300 አመት በፊት በባሪያ ንግድ ጊዜ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ከተቆጣጠሩ በሁዋላ ህዝብን አሸብረው እና ፈሪ አድርገው በራሱ ሃገር እና በራሱ ቀዬ ፈርቶ እና አንገቱን ደፍቶ እንዲታዘዛቸው ለማድረግ እና ለመበዝበዝ ከገደሉ በሁዋላ እሬሳውን መንገድ ለመንገድ ይጎትቱት  ነበር ታድያ አሁንም የማስታውሳቹ ነገር ቢኖር እነዚህ በዘር በሃይማኖት በባህል በቀለም የማናውቃቸው ባእዳን ናቸው᎓᎓ የእኛን ለየት የሚያደርገው በእዚህ ዘመን መሆኑ እና በሃገራችን ውስጥ በህግ አስተዳድራለው በሚል አውሬ መንግስት የተፈጸመ መሆኑ ነው የኦሮሞ ህዝብሆይ ለእኛ ነጻነት ከእኛ ውጭ ማንም ሊመጣልን አይችልም ከዚህ በላይ ወርደት የለም ይህንን አውቀን ትግላችንን እንቀጥል በወንድሞቻችን ሞት ማዘን ብቻ ምንም ፋይዳ የለውም ይልቅ ለተሻለ ትግል እንነሳ እላለሁ᎓᎓

No comments:

Post a Comment