Wednesday 15 October 2014

የቀድሞ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በተመሰረተበት 3 ክሶች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ብሎታል


የፌዴራል አቃቤ ህግ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጣዋ የምትታተምበትን ማሰተዋል ህትመትና ማሰታወቂያ ስራ ደርጅትን ነው 4 ክሶች የመሰረተባቸው።
ከ አንድ እስከ ሶስት የተዘረዘሩት ክሶች በዋና አዘጋጁ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የተጠቀሱ ሲሆን 4ተኛው ክስ በድርጅቱ ላይ ነው።
ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በሀይልና በአመፅ እንዲፈርስና አመፅ እንዲቀሰቀስ አድርጓል የሚለው የክሱ ዋነኛ ጭብጥ ነው በተመስገን ላይ የቀረበው።
በቅፅ 04 ቁጥር 149 ነሀሴ 23 2003 በተሰራጨው እትም ሞት የማይፈሩ ወጣቶች በሚል ርእስ በተከሳሽ ተመስገን ደሳለኝ አመንጪነት በወጣወ እትም፥ ወጣትነት እና አብዮተኛው ለውጥ ነው ድፍርት ነው በማለት በመንደርደሪያነት የአፄ ሀይለ ስላሴ ስርአት ወጣቶች እንዴት አነዳፈረሱትና አሁን ያለው ስርአትም አፋኝና ጨቋኝ መሆኑን ገልፆ የሆነው ሆኖ ብታዩ ሞት የማይፈሩ ወጣቶችን አግኝተናል የሚለውም በ1ኛው ክስ ላይ በተከሳሹ የተፃፈ ነው።
በአፄ ዘመን ወጣትነት አብዮት እንደሆነ አይቻለው በማለት በሰሜን አፍሪካ እና በአረቦች የተነሳውን ግጭት በምሳሌነት ጠቅሷል።
በዚህ እትም ወጣትነት ለውጥ እንደሆነ ወጣትነት ታሪክ የሚሰራበት ወቅት መሆኑንም ጠቅሷል።
በአረብና ሰሜን አፍሪካ የተከሰተውን የህዝብ አመፅ በኢትዮጵያ እንዲተገበር ወጣቶች አደባባይ ለአመፅ አንዲወጡ ቀስቅሷል።
በዚሁ ጋዜጣ በቅፅ 05 ቁጥር 177 የካቲት 23 2004 በተሰራጨው እትም የማይፈራ ይመለስ የሚለውም ፅሁፍም ሌላኛው ነው።

ሞት የማይፈሩ ወጣቶች በሚል ባሰራጨው ፅሁፍ እንደማጣቀሻነት በመግለፅ ወጣቶች ሆ ካሉ ማንንም ምንም እንደማይፈሩ አስታውሶ በአሁኑ ወቅት ያለውን የኢትዮጵያ ሁኔታ ከመፍራት ይልቅ እንድትቆጣ የሚገፋፋ ነው በማለት በሀገሪቱ ያሉ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ችግሮችን ካብራራ በኋሏ የኢትዮጵያ ህዝብ አደባባይ ሆ ብሎ እንዲወጣና መንግስትም የህዝቡንና አመፅ ለመግታት ነጭ ለባሾችን አያሰልፍም፤ ነገር ግን አንድ እንጂ ዘጠኝ ሞት እንደሌለና ለዚህም የሆስኒ ሞባረከ አገዛዝን በመግለፁ አቃቤ ህግ በጋዜጣ ህዝቡ በሀገሪቱ መንግስትና ህገ መንግስታዊ ስርአቱ ላይ እንዲያምፅ እንዲሁም ስርአቱ እንዲያፈርስ በጋዜጣው የቀሰቀሰ በመሆኑ በፈፀመው የመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የመሰናዳት ወንጀል ከሶታል።
2ኛው ክስ የሀገሪቱን መንግስት ስም ማጥፋት በሀሰት መወንጀል የሚል ነው።
1ኛ ቅፅ 04 ቁጥር 146 ሀምሌ 22 2003 እትም ላይ የሁለተኛ ዜግነት ህይወት በኢትዮጵያ እስከመቼ ከመጣነው ይልቅ የሚቀረን ይረዝማል በሚል ርእስ መንግስት በተለያዩ ክልሎች የጅምላ ጭፍጨፋ አድርጓል በማለት በሀሰት ወንጅሎታል የሚል ነው።
አቃቤ ህግ በተመስገን ላይ የመሰረተውን 3ኛውን ክስ በቅፅ 5 ቁጥር 179 መጋቢት 7 ቀን 2004 በተሰራጨው ሲኖዶስና መጅሊሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መጥመቂያ በሚል በወጣ ርእስ ላይ ነው በዚህ ፅሁፍ ለንባብ ካበቃው ዝርዝር ጭብጥ የህዝቡን አስተሳሰብ እንዲለውጥ ያደረገ በመሆኑ ለፈፀመው የሀሰት ወሬዎችን በማውራት ህዝቡን በማነሳሳት ወንጀል ነው አቃቤ ህግ የከሰሰው።
አሳታሚ ድርጅቱ ማስተዋል ላይ የፍትህ ጋዜጣ እትሞችን በአሳታሚነት በማከፋፈል የወንጀል ድርጊቱን የቀሰቀሰ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀመው የመገፋፋት ግዙፍ ያልሆነ መሰናዳት ወንጀል ነው የተከሰሰው።
ተከሳሹ ላይ የህትመት ውጤቶች በማሰረጃነት ቀርበዋል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት በወቅቱ መዝገቡን ይመረምር ስለነበር ተከላከል ሲል የሰጠውን ብይን ተከትሎ ተከሳሹ አንድ የሙያ ማስረጃና ሌሎች ሁለት ምስክሮችን አቅርቦ አስምቷል።
1ኛው የሙያ ምስክር የህግ ተመራማሪው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ናቸው።
ጥቅለ ምስክርነታቸው ሙያውን ተግባራዊ አደረገ እንጂ ለአመፅ አልቀሰቀሰም የሚል ነው።
ሁለት ሌሎች ምስክሮችም ሶስቱም ክሶች ሙያዊ ግዴታውን ተጠቅሞ ሰርቷል የሚለውም የምስክርነት ቃላቸውን፤ ከተሰጠው መብት አልፎ የሌላውን መብትና ሞራል በሚነካ መልኩ ከጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ወጥቶ ለአመፅ የሚያነሳሱ ፅሁፎችን ለንባብ አብቅቷል።
የጠራቸው የመከላከያ ምስክሮችም ክሱን አላስተባበሉም በማለት ተመስገን ደሳለኝ ላይ በተመሰረቱ 3ቱም ክሶች ጥፋተኛ ነው ብሏል።
ከ16ኛው የወንጀል ችሎት መዝገቡን ተረክቦ ያጠናቀቀው 9ኛው የወንጀል ችሎት ዛሬ ተመስገን 3ቱም ክሶች አሳታሚው ማሰተዋል ማሰታወቂያና ህትመት ስራዎች ድርጅት በአንድ ክስ የጥፋተኝነት ፍርድ አሰተላልፎባቸዋል።
ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስም ተከሳሹ ማረፊያ ቤት እንዲቆይ ትእዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን ውሳኔ ለመስጠትም ለጥቅምት 17 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

No comments:

Post a Comment