Tuesday 24 June 2014

ሱዳን ውስጥ ስቅላት ተፈርዶባት የነበረችው ሜርያም ተለቀቀች

በሱዳን ሻሪዓ መሠረት ሃይማኖቷን ወደ እሥልምና እንድትቀይር ታዛ እምቢ በማለቷ እንድትሰቀል ተፈርዶባት የነበረችው የክርስትና ዕምነት ተከታይ ሴት ከእሥር ከተፈታች በኋላ እንደገና በቁጥጥር ሥር ውላ እንደገና ተለቅቃለች፡፡

በሱዳን ሻሪዓ መሠረት ሃይማኖቷን ወደ እሥልምና እንድትቀይር ታዛ እምቢ በማለቷ እንድትሰቀል ተፈርዶባት የነበረችው የክርስትና ዕምነት ተከታይ ሴት ከእሥር ከተፈታች በኋላ እንደገና በቁጥጥር ሥር ውላ እንደገና ተለቅቃለች፡፡

ሚሪያምና ቤተሰቧ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበረው ኻርቱም አይሮፕላን ጣቢያ ላይ የነበረ ሲሆን የሱዳን አሜሪካዊ ባለቤት የሆነችው ሜሪያም ኢብራሂም በቅርቡ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ልትጓዝ እንደምትችል አንድ አሜሪካዊ የሕግ ባለሙያ ጠቁመው ነበር፡፡

አይሮፕላን ጣቢያው ላይ ተይዘው የቆዩት ለሰዓታት መሆኑንና የተያዙትም ከመጓጓዣ ሠነዶቻቸው ጋር ለማጣራት እንጂ እሥራት አልነበረም ሲሉ የሱዳን ባለሥልጣናት የገለፁለት መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ቤተሰቡ ከሱዳን በሰላም እንዲወጣ ለማድረግ እየሠራ መሆኑንም ኻርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
http://amharic.voanews.com

No comments:

Post a Comment