Thursday 12 December 2013

የኢትዮጵያ ሙስሊም መሪዎች የፍርድ ሒደት

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ጥርጣሬ ካሰራቸዉ የኢትዮጵያ የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች፥ አባላትና ተባባሪዎች መካካል አስራ-ሁለቱ በነፃ እንዲለቀቁ ተወሰነ።

ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በነፃ ካሰናበታቸዉ ተከሳሾች መካካል የቀድሞዉየሲቪል ሠርቪስ ሚንስትር የአቶ ጁኔዲ ሳዶ ባለቤት እና ሁለት ድርጅቶች ይገኙባቸዋል።የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጋእንደገለፁት ፍርድ ቤቱ በሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ላይ የተያዘዉን የወንጀል ጭብጥም «ከአሸባሪነት» ወደ «ሽብር አነሳሽነት» እናተባባሪነት አቅልሎላቸዉል።የቀሪዎቹን ጉዳይ ለማየት ፍርድ ቤቱ ለመጪዉ ጥር ሃያ-ሁለት ቀጠሯል። አቶ ተማምን ነጋሽ መሐመድበስልክ አነጋግሯቸዋል።
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

No comments:

Post a Comment