Monday 13 May 2013

የህዝብ አስተያየት፣ የሙስና እስርን አስመልክቶ


ሰሞኑን በወያኔዎች ቤት ብዙ ነገር እየሰማን ነው ። በተለይ ከሙስና ጋር በተያያዘ ጉዳይ ። ነገር ግን በዚህ ሙስና በሚባለው ጉዳይ የሚሰራ አንድ ድርጅት አለ ” ጸረ ሙስና ” የሚባለው ማለት ነው ። ይህ መስሪያ ቤት ከወያኔ የፋሽስት ስርዐት ለማፈንገጥ የሚሞክሩን ወይም ከዚህ የማፊያ ቡድን የተለየ ሃሳብ አመጣለሁ ለሚሉትን ወደ ከርቸሌ መወርወሪያ መስመር ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው የወያኔ ባለስልጣን ሆኖ በሙስና ያልተዘፈቀ የለም ። ይህም መረጃ በጸረ ሙስና ቢሮ እጅ ይገኛል ። ወያኔ ማሰር ሲፈልግ በስልጣን እያሉ የተጨማለቁበትን የሙስና ጉዳይ መዘዝ በማድረግ ግለሰቦቹን ለማሸማቀቅ ብሎም ሌሎች ሙሰኞችን አድርጉ የተባሉትን ህሊናቸውን ሺጠው ህዝብን ማሰቃየትን ሳያቅማሙ እንዲቀጥሉ ለማስጠንቀቅ የተመሰረት መስሪያ ቤት ነው ። ይህ “ጸረ ሙስና “የሚባለው መስሪያ ቤት እንደ ስሙ ቢሆን አፈ ጉባኤው አባዱላ ገመዳ ታራሚ መሆን ሲጠበቅበት ለሙስና ክስ ምስክር ይሆን ነበር??? ሌላው የሙስና እናት አዜብ መስፍን እያለች ባጃጅ ሙሰኞች ቀድመው ይያዙ ነበር??? ለነገሩ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም የዘራውን ያጭዳል ! ለሁሉም ጊዜ አለው! Yessuf Abdo (Facebook)
የባለስልጣናት ሚስቶችን፣ ዘመዶችና ወዳጆችን በተቋሞቻቸው ውስጥ በማይመጥኑት ሃላፊነት በመመደብ፣ ከተለያዩ የማማለያ ሽልማቶች ጋር ከፍተኛ ደሞዝ በመክፈል፣ አንዳንዴም ውጪ አገር ድረስ የህክምና ወጪ በመሸፈን ሰበብ የአገሪቱን የአመራር በትር ጨብጠው አገሪቱን እያለቡ ያሉት ወገኖች በይፋ እንደሚታወቁ የሚገልጹ ክፍሎች “አሁን ተጀመረ የተባለውና ይፋ የተደረገው የሙስና ትግል እነዚህን ክፍሎች ብብቱ ስር ይዞ የሚቀጥል ከሆነ ከቀልድ አይዘልም” ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ያስቀምጣሉ። ጎልጉል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ስለመንግሥት ሌቦች እየተናገረ ነው፤ ሌቦቹን ግን እሱም አያውቃቸው፤ እነሱም እየሰሙት አይደለም፤ የመንግስት ሌቦች የተባሉት የሚግጡባቸው ዋናዎቹ መስኮች ታክስ፣ መሬትና የንግድ ውድድር መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጾአል፤ ከዚህም በላይ የተባሉትን የሌብነት መስኮች ከለምነት ወደበረሃነት ለመለወጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ኃላፊነት አለበት ያለ መሰለኝ፤ ሥልጣን ሳይኖር ኃላፊነት ከየት ይመጣል? እንግዲህ የፌዴራል ፖሊሱንና ሌላውን አልፎ፣ የደኅንነቱን ሰራዊት አልፎ፣ የጸረ-ሙስና ኮሚሽንን አልፎ፣ ዓቃቤ ሕግን አልፎ ሕዝብ እነዚያን ለምለም መስኮች ማድረቅ እንዴት ይችላል? ሌቦቹ ያሉት በመንግስት ጎራ ብቻ ሳይሆን በህዝብም ጎራ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቆም አድርጎአል፤ እንዲህ ከሆነ ‹‹አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ›› የሚባለው ሁኔታ ሰፍኖአል ማለት ይመስላል፤ ይህ እውነት ከሆነ ሌብነት ሥርዓት ሆኖአል ማለት ነው። (ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም) ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
መላኩ ፈንታ በባህርዳሩ ስብሰባ ላይ ‹‹የህወሓት ስውር እጆች›› እንደሚደግፋቸው የሚነገርላቸውን ሁለት መቶ ነጋዴዎች በስም ጠቅሶ ‹‹አላሰራ አሉኝ፤ አስቸገሩኝ!›› ብሎ ሪፖርት ማቅረቡ ያስቆጣው አካል በእስሩ ላይ መኖር አለመኖሩን፤ አዜብ መስፍን በዛው ጉባኤ ላይ ‹‹መለስ ብቻ ነው በደሞዝ የኖረው›› የሚል ጥቆማ ከማቅረቧ ጋር ተያያዥነት አለው ወይስ የለውም? (ተመስገን ደሳለኝ)ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
“የትናንቱ እስር ከሙስናው ጉዳይ ይልቅ ፖለቲካው ድምፀቱ ነው የሚሰማኝ”
ሰሞኑን ኢትዮጵያ ከነበረው ዜና ውስጥ ሕዝቡን እያነጋገረ የነበረው የዋናው ኦዲተር ሪፖርት ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት፣የአሰራር ዝርክርክነት እና ለምን እንደተከፈሉ የማይታወቁ ክፍያዎች በመንግስት መስርያቤቶች ላይ መኖራቸውን የ 2004 ዓም የሂሳብ ምርመራ ሲያደርግ እንደረሰበት ለምክርቤት ባቀረበው ሪፖርት መግለፁ ነበር። (ጌታቸው፣ ከኦስሎ) ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

No comments:

Post a Comment