Thursday 30 May 2013

የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት ድህረ ገጾችን ለማፈን 26 ቢሊዮን ብር ክፍያ ለቻይና መንግስት ፈጸመ

ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከአስተማማኝ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ የደህንነት ሰራተኛ ባገኘው መረጃ መንግስት ለስርአቱ አደጋ ይሆናሉ ብሎ የገመታቸውን የመገናኝ ብዙሀን ወደ አገር ቤት ሰርገው እንዳይገቡ ለመከላከል ከ1.2 ቢሊዮን ዶላር ወይም ወደ 26 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ መክፈሉን ለማወቅ ተችሎአል።
በቁጥር አንድ እንዲታፈን ትእዛዝ የተላለፈበት ኢሳት ሲሆን ድህረገጹ ራዲዮው እና ቴሌቪዥኑን ሙሉ በሙሉ  እንዲታፈን ስምምነት ላይ ተደርሷል።  ፣ የአሜሪካ ድምጽ  እና የጀርመን ድምጽ የራዲዮ ጣቢያዎች ደግሞ በሚያቀርቡት ዝግጅት ይዘት አይነት አፈና እንዲካሄድባቸው ሲወሰን አሁንም ድረስ ስርአቱን የሚጻረሩ ድረጎች ሙሉ በሙሉ እንደታፈኑ ይገኛሉ።
ኢሳት ድረገጹ ቢታፈንበትም ራዲዮ እና ቴሌቪዥኑ ካለፉት 5 ወራት ጀምሮ ያለ ምንም ችግር እየተላለፈ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ህዝብ የዲሽ አቅጣቻውን በየጊዜው በመቀያየር ኢሳትን በመከታተል ላይ ይገኛል። አንድንድ ባለስልጣናትም ኢሳትን እየተከታተሉ አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመራቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ።
በተመሳሳይ ዜናም መንግስት በፊስ ቡክ እየደረሰበት ያለውን ውግዘት እና የለውጥ ማእበል ለመግታት ‹‹ ሬሳው ›› ሲል ስም የሰጠውን የአፈና ቴክኖለጅ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ሙከራው ተግባራዊ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ የፊስ ቡክ ግንኙነቶችን ለመገደብ እድል እንደሚያገኝ የደረሰን መረጃ ያሳያል። ካለፈው ወር ጀምሮ ስራውን ለማስጀመር የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት አለመሳካቱ ታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

Ethiopia to Accommodate Nations Concerned by Nile Dam

Note: This tug of war is going on until Debretsion or his like is bribed by Egypt or some one is fulfilled with his/her hidden agenda.

grandrenaisence
The Grand Ethiopian Renaissance Dam will be twice the size of Singapore
May 30, 2013 (Bloomberg) — Ethiopia’s government said it will try to accommodate nations concerned that their water supplies may be affected by the damming of the Blue Nile River, as Sudanese and Egyptian officials met to discuss the issue.
Ethiopia, source of one of the two tributaries of the Nile River, will start filling the Grand Ethiopian Renaissance Dam on the Blue Nile at the “end of next year,” Deputy Prime Minister Debretsion Gebremichael said in an interview yesterday. The 80 billion-birr ($4.3 billion) hydropower project may begin generating of electricity next year and is set for completion in 2017, he said.
The schedule for filling the 74 billion cubic meter reservoir is expected to be a “major comsg4ncern” for the downstream nations of Egypt and Sudan, said Debretsion. Once completed, the power plant will be Africa’s largest with the capacity to generate 6,000 megawatts. Egypt, which relies on the Nile for almost all of its water, has historically opposed upstream projects on the world’s longest river.
“We are not selfish, we are not only looking at our national interest,” said Debretsion, who is also chairman of the state-owned Ethiopian Electric Power Corp. “This is an international river and we will try our best to accommodate their benefits and their interests.”

የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን በኅብረት ስራ ጀመሩ!

ዓርብ የፖለቲካና የሙስሊም እስረኛ ጠበቆችን ያነጋግራሉ

aba nsmne


በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተ የአሜሪካን የህግ ባለሙያዎች ማህበር (ABA – American Bar Association) ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ አርብ እንደሚጀምር ተገለጸ። አዲስ አበባ ካሉ የፖለቲካና የሙስሊም ወገን እስረኞች ጠበቆች ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ አርብ ግንቦት 23፤2005ዓም ያደርጋሉ። አቶ ኦባንግ ሜቶ የተረሱ እስረኞች ጉዳይም እንደሚካተት ጠቅሰው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለታሰሩ ዜጎች ጥብቅና የቆሙ ካሉ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ በቀጥታ እንዲገናኙ ጥሪ አቅርበዋል።
(ABA) በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከ400 ሺህ በላይ የህግ ባለሙያ አባላት አሉት። ይህ በአሜሪካ ትልቅ የተባለ ማህበር በግፍ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ በይፋ የድጋፍ ጥያቄ ባቀረቡ በቀናት ውስጥ ሲሆን፣ በጋራ በተከናወኑ ንግግሮችና የሰነድ ውይይቶች በወር ጊዜ ውስጥ ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል።

Monday 27 May 2013

የኢህአዴግና የሻዕቢያ ድርድር ተበጠሰ

ኢሳያስ፣ ደሚት፣ ግብጽ፣ ኳታር፣ ኢህአዴግ

haile and esayas


ኳታር በተናጠል የጀመረችው ኢትዮጵያንና ኤርትራን የማሸማገል ሂደት መበጠሱ ተሰምቷል። ከሽምግልናው ዙሪያ የግብጽ ሚና ስለመኖሩ አመላካች ጉዳዮች አሉ እየተባለ ነው። በድርድሩ ኢህአዴግ በዋናነት እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠው የትግራይ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደሚት/ ጉዳይ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
አቶ መለስ የኢትዮጵያን ወደብ እንደተራ ጉዳይ አሳልፈው በመስጠት ኤርትራን እንደ አገር እውቅና በሰጡበት ወቅት ድጋፍ ለማሰማት ቀዳሚ የነረችው ኳታር ከበረሃው ትግል ጀምሮ የሻዕቢያ ወዳጅ አገር እንደሆነች ይታወቃል።
ከዚሁ የከረመ ወዳጅነት በመነሳት ኳታር በ2008 ከኢህአዴግ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን የጸብ ግድግዳ አፍርሳ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው በዋናነት ሁለቱን አገሮች መልሶ ለማስታረቅ በተያዘ እቅድ ስለመሆኑ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ይናገራሉ። በተለይም አሁን ያለው የኤርትራ አስተዳደር እጣ ፈንታ አብዝቶ ያስጨነቃት ኳታር በኤርትራ ወደብ ሊዝ በማድረግ፣ ኢንቨስትመንት ላይ በመሳተፍና ልዩ ድጎማ በማድረግ ቀዳሚውን ስፍራ ስለምትይዝ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ላይ ታች ማለቷ እንደማይደንቅ ስምምነት አለ።
ጎልጉል ምንጭ የሆኑ ዲፕሎማት እንዳሉት ኳታር አሁን እርቁን የፈለገችው በኤርትራ መረጋጋት እንዲፈጠርና የኤርትራ ኢኮኖሚ አንዲያገግም ለማድረግ በሚል ነው። በሌላ በኩል ህወሃት የዘወትር ስጋቱ የሆነውን ሻዕቢያን ለማስወገድ ሌት ከቀን እንደሚሰራና ይህም በድርጅት ደረጃ አቋም የተያዘበት ጉዳይ በመሆኑ የኤርትራ መንግስት መሰረታዊ የአቋም ለውጥ ሳያደርግ ከኢህአዴግ ጋር የድርድር ስምምነት ላይ መድረስ አስቸጋሪ እንደሚሆን ሁሉም ወገኖች የሚረዱት ጉዳይ ነው።

Sunday 26 May 2013

Saturday 25 May 2013

ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

(ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. / May 24, 2013)

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ከተመሠረተ 2007 እ.አ.አ ጀምሮ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናትን የምዕራቡ ድንበራችን እርዝማኔው 1600 ኪ/ሜትር የጎን ስፋቱ ከ30 እስከ 60 ኪ/ሜትር የሚሆነውን ከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብትና ልዩ ልዩ ብርቅየ የዱር አራዊትና አውዋፍ የሚገኙበት አንጡራ ለም የድንበር መሬታችንን ፀረ-ኢትዮጵያው ወያኔ የገዥ ቡድን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት በምስጢር መደራደሩን ፤ ከዚያም በኋላ መስጠቱን ለሕዝብ በማጋለጥ በተከታታይ ሰፊ መግለጫዎች ማውጣቱ፤ ለልዩ ልዩ የዜና አውታሮች ቃለ-ምልልሶች መስጠቱ እና የተለያዩ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ማካሄዱ የሚታወስ ነው። ከዚህም በላይ፤ ይኽኑን አሳሳቢ የድንበር ጉዳይ በተመለከተ ስፋትና ጥልቀት ያለው ታሪካዊ ሠነድ እንደሚያዘጋጅ ቃል መግባቱ የሚታወቅ ነው።
በዚሁ ቃል-ኪዳን መሠረት፣ ከሁለት ዓመት በላይ ሰፊ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ሲያካሂድ ቆይቶ፤ ይህኑን ዓብይ ጉዳይ በተግባር ለማዋል እንዲችል፤ የድንበሩ ኮሚቴ ከፍተኛ አካል የሆነው ምክር ቤት ግንቦት 10 እና 11 ቀን 2005 ዓ.ም. ( May 18 and 19, 2013 ) ታላቅ ጉባዔ በሲሊቨር ስፕሪንግ ከተማ፣ ሜሪላንድ፣ አሜሪካ (Silver Spring, Maryland, USA) አካሂዷል።

Friday 24 May 2013

ሰበር ዜና፣ የሰማያዊ ፓርቲ የግንቦት 17ቱን ሰልፍ ወደ ግንቦት 25 አስተላለፈ


ECADF – የሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ሲል ጠርቶት የነበረውን የሰላማዊ ሰልፍ በተመለከተ ለአዲስ አበባ አስተዳደር በደብዳቤ ለማሳወቅ በሞከረበት ወቅት የከተማው አስተዳደር ሀላፊዎች ሆን ብለው ደብዳቤውን አንቀበልም በማለታቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የአይን እማኞች በተገኙበት ደብዳቤውን በአንዱ የከተማው አስተዳደር ቢሮ ውስጥ እጠረጴዛ ላይ አኑረው እንደወጡና በህጉ መሰረት የሰላማዊ ሰልፉን ከጠራው አካል በኩል መደረግ ያለበት ሁሉ ስለተደረገ ፓርቲው በያዘው ፕሮግራም መሰረት ሰልፉን ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት እንደሚያካሂድ አሳውቆ ነበር።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰልፉን ፈቀደ
የሰማያዊ ፓርቲ ስለ ሰላማዊ ሰልፉ ለአዲስ አበባ አስተዳደር በደብዳቤ ለማሳወቅ በሞከረበት ወቅት ደብዳቤውን ለመቀበል አሻፈረኝ ብለው ሲያንገራብዱ የዋሉት የከተማው አስተዳደር ሀላፊዎች ዘግይተው የሰማያዊ ፓርቲ ባሳወቀው ቀንና ቦታ ሰልፉን ሊያካሂድ እንደሚችል ለፓርቲው በቀጥታ በተጻፈ ደብዳቤ አሳወቁ (እኛም የዚህን ደብዳቤ መልዕክት በሰበር ዜና ይዘን ወጥተን ነበር)። የሰማያዊ ፓርቲም ይህንኑ ደብዳቤ እንደተለመደው በፌስ-ቡክ ገጹ ላይ አትሞታል። (የደብዳቤውን ይዘት ለመመልከት እዚህ ይጫኑ።)

የደህንነት ሹሙ ስዊድን ይመጣሉ


አዲስ አደረጃጀትና አዲስ ሬዲዮ በስካንዲኔቪያ

eprdf1


በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security Service) የብሔራዊ ደህንነትና የደኅንነት አገልግሎት ሁለተኛ ሰው የሆኑት አቶ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ ስዊድን እንደሚመጡ ተሰማ። በስካንዲኔቪያ አገራትና በድፍን አውሮፓ በሚኖረው ዲያስፖራ ላይ የሚያተኩር “የግል” መሰል የሬዲዮ ስርጭት ለመጀመር መታሰቡም ተሰምቷል።
የጎልጉል የመረጃ ምንጮች እንዳስታወቁት አቶ ኢሳያስ ስዊድን ይመጣሉ የተባለው በመጪው የሰኔ ወር ነው። የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸውና አቶ መለስ በእጅጉ ይተማመኑባቸው እንደነበር የሚነገርላቸው አቶ ኢሳያስ ስዊድን ከደረሱ በኋላ ሊያከናውኑ ስላሰቡት ተግባር ዝርዝር ለመረዳት ጊዜው ገና እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል።
“ሆኖም ግን” ይላሉ ምንጮቹ፣ ” ሆኖም ግን አቶ ኢሳያስ ድርጅታቸው ኢህአዴግ በስካንዲኔቪያን አገሮች በተደጋጋሚ ያጋጠመውን ውግዘት አስመልክቶ አዲስ አደረጃጀት እንደሚገነቡ ታውቋል፡፡”
የኢህአዴግና የስርዓቱ ደጋፊዎችን ለማብዛት በልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅም አባላትን የመመልመሉ ስራ በተጠናከረ መልክ እንደሚሰራበትና የዲያስፖራውን ማኅበረሰብ ለመጠርነፍ ይዋቀራል የተባለው አዲሱ ድር /ኔትወርክ/ ትኩረት የሚያደርገው “አብዛኛው አድፋጭ” ወይም “silent majority” ላይ እንደሆነ መረጃ ሰጪዎቹ ተናግረዋል። ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲዎችን ማደራጀት አንዱና ዋናው የአደረጃጀቱ አግባብ እንደሆነም ተጠቁሟል።
ቀደም ሲል በስካንዲኔቪያን አገራት የዲያስፖራ ድር /ኔትወርክ/ በበላይነት ይመሩ የነበሩ የደህንነት ሰው ተጠርተው ይሁን በፈቃዳቸው ወደ አገር ቤት መሄዳቸውን ያመለከቱት የመረጃው ምንጮች፣ እኚሁ ሰው በአገር ቤት ቆይታቸው በስካንዲኔቪያ ስላለው የዳያስፖራ ሁኔታ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ አመልክተዋል።

Thursday 23 May 2013

ኦባንግ ለኬሪ የጥሪ ደብዳቤ ላኩ!


አኢጋን ለታቀደው ሰልፍ ድጋፍ ሰጠ

smne state


በቅርቡ በሚከበረው 50ኛው ዓመት የአፍሪካ ኅብረት ክብረበዓል ላይ በተጋባዥነት ለሚገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በፋክስ የሚደርስ ቀጥታ ደብዳቤ ላኩ፡፡ በደብዳቤው ላይ አቶ ኦባንግ ሰሞኑን በአፍሪካ ህብረት አካባቢ ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድርጅታቸው ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
በበርካታ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለሚ/ር ኬሪ በደብዳቤያቸው ላይ ማሳሰቢያ የሰጡት ኦባንግ የአፍሪካ ኅብረት ሲቋቋም ቅኝ አገዛዝን መታገል፣ የህግ የበላይነትን ማስከበርና የዜጎችን መብት ማስጠበቅ ዋንኛ ዓላማው የነበረ ቢሆንም የያኔዎቹ መስራች መሪዎች አሁን በህይወት ቢኖሩና የዛሬዪቱን አፍሪካ ቢመለከቱ ምን ይሉ ይሆን በማለት ጠይቀዋል፡፡
በመላ አፍሪካ በዘመናችን ያለውን የሰብዓዊ መብት መጣስ፣ የሙስና መስፋፋት፣ የሕግ የበላይነት መጥፋት፣ … የጠቀሱት ኦባንግ በኢትዮጵያ የተንሰራፋውንና በዘረኝነት ላይ የተመሠረተውን የአገዛዝ ስልት፣ አፈና፣ ፍትህ አልባነት፣ ህገወጥነት፣ በፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ላይ የሚደርሰውን እንግልት፣ በምርጫ ሰበብ የሚደረገውን ዓይን ያወጣ ማጭበርበር፣ ከውጭ የሚገባ ዕርዳታን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀምን፣ በጋዜጠኞችና ሃይማኖት መሪዎች ላይ የሚደርሰውን እስርና አፈና፣ ወዘተ ዘርዝረው በመጥቀስ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስረድተዋል፡፡

Monday 20 May 2013

የበረከትና አላሙዲ ልሳን (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


ከኢየሩሳሌም አርአያ

በአላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት፣ በረከት ስምኦን ከጀርባ የሚመሩት እና በአንድ ኤርትራዊ የሚዘጋጀው ጋዜጣ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር ሲሞክር መታየቱን ተከትሎ ምስጢሩን የሚያውቁ የቅርብ ምንጮች ጉዳዩን አጋለጡ። « ሰንደቅ» የተባለውና በነፃ ፕሬስ ስም የሚያደናግረው ጋዜጣ ፍሬው አበበ በተባለ ዋና አዘጋጅነት እንዲሁም በኤርትራዊው ፋኑኤል ክንፉ ምክትል ዋና አዘጋጅነት የሚሰናዳ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሲሆን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በውድ ዋጋ ቢሮ ተከራይቶ እንደሚሰራ ያስታወቁት ምንጮቹ አያይዘውም ፍሬው አበበ ከዚህ ቀደም የብአዴን ልሳን በሆነው « ማህቶት» ጋዜጣ ላይ ይሰራ እንደነበረና ከብአዴን አመራር አባላትም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው አረጋግጠዋል። በፓርቲው ልሳን ለመስራት ደግሞ የድርጅቱ አባል መሆን ግድ እንደሚል የጠቆሙት ምንጮቹ “ጋዜጠኛ” ፍሬው የፓርቲው አባል እንደሆነና በነበረው ታማኝነት በበረከት ስሞን ተመርጦ አሁን ባለበት ጋዜጣ እንዲሰማራ መደረጉን አስታውቀዋል። በተጨማሪ  «የኢትዮጲያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር» ተብሎ በሚጠራውና የገዢው ፓርቲ ተለጣፊ በሆነው “ማህበር” ጋዜጠኛ ፍሬው የቦርድ አባል ሲሆን፣ ይህ ማህበር በሃገሪቱ ነፃ ፕሬስ እንዳይኖር ቀን ከሌሊት የሚተጋ ነው ሲሉ ምንጮቹ በመግለፅ ተከታዩን ማስረጃ ያቀርባሉ። « ማህበር ተብዬው በሚሚ ስብሃቱ ሬዲዮ በኩል « እነእስክንድር ነጋ አሸባሪ ናቸው» ብሎ ተከራክሯል፤ «አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስ» ጋዜጦች ሲዘጉ «ከስረው ነው» በማለት የሽመልስ ከማልን መግለጫ የሚያጠናከር መግለጫ በማውጣት ከመንግስት ወግኖ ተሟግቷል፤ እንዲሁም በተመስገን ደሰላኝ ይዘጋጁ የነበሩት «ፍትህ፣አዲስ ታይምስና ልዕልና» ጋዜጦች በነበረከት ቀጭን ትእዛዝ እንዲዘጉ ሲደረግም የነፍሬው ማህበር ተመሳሳይ አቋም በማራመድ መከራከሩን በዋቢነት የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም፥ በአጠቃለይ ጋዜጠኛ ሲታሰር፣ ሲንገላታና ሲሰደድ ልክ መንግስት ተቀጥላ እየፈጠረ ለመወንጀል እንደሚሞክረው ሁሉ ይህም ማህበር ተመሳሳይ አካሄድ የሚከተል ፀረ-ፕሬስ ስብስብ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ የዚህ ተለጣፊ ማህበር ሊቀመንበር አንተነህ አብርሃም እንደሆነ የጠቆሙት ምንጮቹ የአንተነህ ታላቅ ወንድም አማኑኤል አብርሃ ሲባል የደኢህዴን/ኢህአዴግ ማ/ኮሚቴ አባል መሆኑን አጋልጠዋል።
በሌላም በኩል ምክትል የጋዜጣው አዘጋጅ ኤርትራዊው ፋኑኤል አንድ ሰሞን በኢቲቪ የህትመት ዳሰሳ ላይ ቀርቦ « የኢህአዴግ ደጋፊ ነኝ » ሲል በይፋ መናገሩን ያስታወሱት ምንጮቹ የስርአቱን ትክክለኛነት በመግለፅና በመከራከር የገዢው ፓርቲ «ቋሚ ጠበቃ» ሆኖ መታዩትን ጨምረው ገልፀዋል። (ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ የነበረው አቤ ቶክቻው « የኢቲቪ አምደኛ» ሲል በወቅቱ ተሳልቆበታል)..

Sunday 19 May 2013

የ“ቀዩ መስመር” ሰላባዎች?


የ"ማበስበሱ" ቁማርና የደኅንነቱ ሚና!!

red-tape2


መለስ ህይወታቸው እንዳለፈ ከተሰጡት አስተያየቶችና ትንቢቶች መካከል ቀዳሚው የመለስ ሞት ለህወሃት ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ መሆኑ ነበር። በዚሁ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግ ዲፕሎማት “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ይህ እንደሚከሰት ቁልጭ አድርገው ተናግረው ነበር።
መለስ አፍነው የያዟቸው የፖለቲካ ችግሮች ጊዜያቸውን እየጠበቁ የሚፈነዱና በመጨረሻም ፓርቲውን እንደሚፈረካክሰው የተገለጸው በየደረጃ የሚፈነዱት ችግሮች እየበረከቱ በመሄዳቸው ነበር። መለስ አፍነው የያዟቸው ችግሮች የእርስ በርስ መበላላት ደረጃ እንደሚያደርሱ በርካታ ወገኖችና መገናኛዎች ጎልጉልን ጨምሮ አመላክተዋል። አሁን አሁን ትንቢቱ የፍጻሜው ጅማሬ ላይ እንደሚገኝ የሚናገሩም አሉ።
የፖለቲካ አቋም ልዩነት ሳይኖር የአስተሳሰብ ልዩነት ማራመድ በህወሃት ዘንድ አይቻልም። ከተሞከረም ክህደት ነው፤ መፈንቅለ መንግስት የማካሄድ ያህል ነው። የርዕዮተ ዓለም ለውጥ የማቀጣጠል ያህል ያስፈርጃል። ሽብርተኛ ያስብላል። ከቶውንም ተቀባይነት ስለሌለው ድንበር ተበጅቶለታል። ድንበሩም “ቀይ መስመር” በመባል ይታወቃል። የ”ቀይ መስመር” ሃሳብ አመንጪና ደራሲ አቶ መለስ ናቸው። “በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ” በሚል የምጸት ስም የሚጠሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም ይህንን የቀይ መስመር ጽንሰ ሃሳብ ለንግግር ያህል ይጠቀሙበታል።

Thursday 16 May 2013

The Evil Strategies of Land Grabbing in the Southern Part of Ethiopia


By Assefa Getachew | May 16, 2013

The historical impacts of land-grab in Ethiopia were characterized by brutal conflicts, cultural
extinction, and even genocide through mass killings. The war of occupation and land-grab in the
last decades of the nineteenth century resulted in the death of about five million people in
Southern Ethiopia (OSA 2013). The current problems associated with land-grab are especially
complex in Southern Ethiopia; the local people are not represented in the government of Ethiopia
that is dominated and led by TPLF. Mistrust between TPLF leaders who come from the North
and the Southern peoples of Ethiopia is rampant, shaped by a bitter history of war, occupation,
cultural domination, and inherited hostility. The non-Tigrayan population of Ethiopia sees the
decision of the TPLF regime as a deliberate and conniving move to dismantle the cultural fiber
of the South and expand Tigrayan cultural and economic domination. Land-grab is indeed
perceived among the Southern Ethiopian population as a hostile trap targeting their most sacred
property, their land.
Since 1996, the total area of agricultural land transferred to the investors is more than 5 million
hectares. A total land transferred to investors will be 10 million hectares of agricultural land by
the end of 2015 (OSA 2013). Over 94% of the land assigned to TPLF officials and foreign
investors is located in Southern Ethiopia (ibid). To seal the deal, the government developed ‘a
conniving and exploitive strategy’ and to implement this, it made policy decisions and then
signs land lease contracts on behalf of the peoples of the Southern Ethiopia. The policy
thoroughly comes from the TPLF leaders who are ethnic group of the North

የሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ዝግጅት እያደረገ ነው


የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ባስተላለፈው መሰረት አመራሮቹ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆኑ ገለጹ።

Ethiopian blue party, semayawi party
ፓርቲው “በመንግስት ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ ለመፈለግ…” በሚል ባስተላለፈው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት ድምፃችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ያነሳናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበራትና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእነዚህ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ” ሲል አሳስቧል።
ይህ በዚህ እንዳለ በፌስቡክ፣ ፓልቶክና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛ መረብ (social media) ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን ለተጠራው የሰላማዊ ሰልፍ ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን የፌስቡክ ፎቶዎቻቸውን በጥቁር የሰው ምስል በመቀየር ድጋፋቸውን እያሳዩ ሲሆን የፓልቶክ መወያያ መድረክ ታዳሚዎች ደግሞ ጽሁፎቻቸውን በጥቁር ቀለም በመቀየር ሰማያዊ ፓርቲ ጥቁር ልበሱ ሲል ያስተላለፈውን መልዕክት ተግባራዊ እያደረጉ ነው።

OSA’s Appeal Letter to the UN Secretary General Ban Ki-moon about the Conflict in Eastern Oromia, Ethiopia


P.O Box 32391, Fridley, MN 55432
www.oromosudies.org
May 16, 2013
His Excellency Mr. Ban Ki-moon, Secretary-General
Office of the Secretary General of United Nations
885 Second Avenue
New York, NY 10017, USA
RE: OSA’s Appeal Letter to the UN Secretary General Ban Ki-moon about the Conflict in Eastern Oromia, Ethiopia
Your Excellency Ki-moon:
I am writing on behalf of the Oromo Studies Association (OSA), a scholarly organization established by Oromo and non-Oromo scholars to promote studies on and relevant to the Oromo and other people of Ethiopia and the Horn of Africa. The Oromo, the largest ethno-national group in the Horn of Africa, constitute 40% of the Ethiopian population. The coalition of the ruling party which has dominated Ethiopian political landscape since 1991 is controlled by the Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF). The TPLF, which fears Oromo numerical strength in any free and fair election, has systematically destroyed all independent Oromo organizations in Ethiopia. The TPLF even destroyed the Oromo Relief Association, a non-profit organization that assisted the people who were affected by draught and famine.
Sadly, we have learned recently from reliable sources and from our contacts in Eastern Oromia, Ethiopia, that the so called ”Special Police” or “Liyu Police” of the Ogaden Regional State has attacked Oromo communities in Eastern Haragee Zone of Oromia Regional State. The reports are still developing due to the fact that the Ethiopian government denied access to journalists and any independent media to the area. However, we have confirmed through our human rights researchers and through our own contacts that at least 37 individuals either have been killed or made to disappear when the Ogaden Liyu Police raided the counties of Oromia bordering the Ogaden Regional State, mainly Anniya, Jaarsoo and Miesso. An unknown number have been wounded, and an estimated 20, 000 people have been displaced and are in dire situation with no assistance from the government or other non-governmental agencies. It is to be noted that charitable organizations are restricted or in many situations prevented from any movement in the country, especially in Eastern Ethiopia.

Ethiopian Journalist Arrested Over Article About Former Dictator Wife



(VOA News) ADDIS ABABA, ETHIOPIA — An Ethiopian journalist has been arrested and interrogated for writing an article about the wife of late prime minister Meles Zenawi. Wednesday’s arrest came as a surprise since the article was published seven months ago.Former First Lady Mrs. Azeb Mesfin Cared About Rumors
Ethiopian journalist Ferew Abebe, editor-in-chief of the weekly publication Sendek, said he was summoned Wednesday to the Federal Police Crime Investigation Department office. He was interrogated about an article he wrote and published seven months ago and was accused of defaming the former first lady, Azeb Mesfin.
Ferew said he was very surprised about the interrogation and being treated like a criminal. He said the federal police asked him many questions and wanted him to reveal his sources. They then took his fingerprints, personal details and photos before releasing him on $265 bail.
Asked for comment, an official in the Ethiopian prime minister’s office, Getachew Redda, said he has no knowledge about journalists being interrogated for writing rumors about the former first lady.

አንጋፋዋ ድምጻዊ አበበች ደራራ አረፈች



ለረጂም ዓመታት በራስ ቴአትር በድምጻዊነት ስትሰራና ለአድማጮችዋ ዜማዎችን ስታቀርብ ኖራ በስተመጨረሻው ወደ እስራኤል ሀገር ከትማ ስትኖረ የነበረችው ታዋቂዋ ድምጸ መልካሟ አበበች ደራራ ዛሬ ሜይ 16 ቀን ባደረባት ህመም ሳቢያ ሕይወቷ አልፏል፡፡Ethiopian singer Abebech Derara
አበበች ደራራ በሕመም ተይዛ ለበርካታ ወቅት በአልጋ ላይ ከመቆየቷም ባሻገር ጨርሶ ከሰዎች ጋር ግንኙነት አቋርጣ በሽታዋን ለብቻዋ ስታስታምም እንደነበረች በቅርብ የሚያውቋት ይናገራሉ፡፡
የአበበች ደራራ አስከሬን በኖረችበት የቴል አቪቭ ከተማ በዛሬው እለት ከቀኑ 3.00PM ላይ ወደ ቀብር በወዳጅ ዘመዶች ታጅቦ በመሄድ ሥርአተ ቀብርዋም ይፈጸማል፡፡ 
ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትንፈጣሪን ይስጣቸው ዘንድ እለምናለሁ፡፡
አርቲስት ደበበ እሸቱ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳስቀመጠው።

Wednesday 15 May 2013

Diddaan barattootaa Yuunivarsiitii Arbamic mooraa Caamoo jabaate



Caamsaa 16,2013 Arba Minc
Diddaan barattootaa mootummaa garboomfataa Wayyaanee irratti jabaachaa dhufuun Yuunivarsiitii Arbaminc mooraa Caamoo keessatti barattootni hiriira jabaa bahuun mootummaa Wayyaanee balaaleffatan.Mootummaan garboomfataa wayyaanee baajata dhimma barnootaaf kaawame irraa looguun dhimma waraanaaf tolchuun bittaa umrii isaa dheereffachuu irraan darbee nyaata summaaaa fi qulqullina hin qabne dhiyeessuun barattoota fixuuf wayita jirutti irratti dhaqqabamuun diddaan kun taasifamee jira.
Mootummaan garboomfataa wayyaanee gaaffii mirgaa barattootni gaafatan dura dhaabbachuuf federaala hedduumminaan bobbaasuun aara ija gubu itti gadhiisuun barattoota miidhaa fi reebaa kan oole yoommuu tahu diddaan kun daran jabaachuun mooraan Caamoo mooraa waraanaa tahee jira.Mootummaan wayyaanees gamtaan barattootni gaaffii mirgaa kaasuu isaaniitti hedduu kan rifate yoommuu tahu yeroo ammaa basaastota barattoota keessaa

ወያኔ እያዘናጋን ነው እየተዘናጋ? ህዝባዊ ጥያቄ መመለስ መፍትሄ ነው!


ምንሊክ ሳልሳዊ

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ህዝባዊ ጥያቄዎች እየበረቱበት የመጣው ወያኔ መላወሻ በማጣቱ የሚያደርገውን እስካለማወቅ ደርሷል:: ከእነዚህም ድንብርብሮች አንዱ ከአባቱ ሻእቢያ እንደወረሰው የፈጠራ ወሬ በአለም አቀፍ ደረጃ ማሰራጨት ነው:: እንዲሁም የህብረተሰቡን ጥያቄዎች ያስረሱልኛል ጭንቅላት ይሰርቃሉ የሚል እደምታ ያለውን ፈጣን ዘገባ ማሰራጨት ስራዬ ብሎ ይዞታል::addis ababa demonstration
ባለፉት 21 አመታት የአገዛዝ ዘመኑ ወያኔ ስልታዊ የሆኑ ያልሰለጠኑ እና ጫካዊ ብልሃቶችን ለመፍጠር እና ሲነቁበትም አለማቀፍ ሽብርን ይፈጥራሉ የሚለውን ወንጀል በዜጎች ላይ በመላከክ የትግል መሪ ሃሳቦችን ወደ አንድ አቅጣጫ ሊነዳቸው ይፈልጋል:: የህዝቦችን የመብት እና የነጻነት ጥያቄ መመለስ ያቃተው ወያኔ በሚፈጥራቸው የፈጠራ ወሬዎች ህዝቡን ለማደንዘዝ እና ለማዘናጋት እየዳከረ ይገኛል::
የፊተኞቹን ጥለን የቅርቦችን ስናስባቸው የሙስሊሙን ጥያቄዎች ተከትሎ የክርስቲያኑን አንድነት ያየው ወያኔ ተደናግጦ በባህር ዳር ደራሲ በኣሉ ግርማ በምንኩስና ተገኛ በማለት የህዝቡን አትኩሮት ለማሳብ ያደረገው ሙከራ ህብረተሰቡ ፊቱን ወደ ባህር ዳር አትኩሮ ትግሉን እንዲያዘናጋ ያደረገው ሙከራ የከሸፈበት ሲሆን ይህንን ተከትሎም ከፍተኛ ውግዘት ያስከተለውን በቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉትን የኣማራ ተወላጆችን ሁኔታ ለመደባበቅ የሻእቢያ እና የወያኔ የእንግሊዝ ወኪሎች እነ ዘርኣይ በምስራቅ አፍሪካ የተነሳባቸውን የአበሻ ትኩሳት ለመፈንገል ይረዳቸው ዘንድ መንግስቱ ሃይለማርያም ሞተ ብለው በቶፒክስ ድህረገጽ እንዲሁም ለእኛ ለሚያውቁን ደሞ በSMS ላኩና ወሬውን እንድያመለስ አድርገን አስፍተን አራገብነው:: ወያኔ ይታወቃት አይታወቃት አላውቅም እንጂ የህዝቡን ጭንቅላት ለመስረቅ የምታደርገው ጥረት እስካሁን አልተሳካላትን ህዝብ ለ 2 እና 3 ቀናት ሊዘናጋ ይችላል እንጂ ለዘላለም አይዘናጋም:: በርግጥ የትግል እረፍት የለውም ለነሱ የስልጣን ማስረዘሚያ ለጫ ደሞ የትግል እረፍት ሊሆን ይችላል::

አኢጋን ታሪካዊ ያለውን ሰነድ አተመ!

"ባይዘመርላችሁም ጀግኖች ናችሁ"

smne amharic


“በቦታው ላይ ሆናችሁ ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ፤ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልጻችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልጹት ግን አትረሱም። ልትረሱም አትችሉም። ብዙ ባይነገርላችሁና ባይዘመርላችሁም ታላቅ ስራ ሰርታችሁዋልና ክብር ይሁንላችሁ” በማለት አቶ ኦባንግ ሜቶ ምስጋና ያቀረቡለት ታሪካዊ ሰነድ ታተመ።
የስርዓቱ ላንቃ ስር ሆነው የህይወት ዋጋ በመክፈል መረጃ የሰጡትን ወገኖች የአክብሮት ምስጋና በማቅረብ በሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ስም ለጥናቱ ተባባሪዎች ሁሉ ክብር እንደሰጡ የዘገበው የጋራ ንቅናቄው ለሚዲያ ባሰራጨው የፕሬስ ሃተታ ላይ ነው። ንቅናቄው “በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ተተርጉሞ መታተሙን ይፋ ባደረገበት ዜናው ይህ ታሪካዊ ሰነድ ለመጪው ትውልድ በቅርስነት የሚቀመጥ እንደሆነ አመልክቷል።
ኢህአዴግ እዚህ ግባ ሊባል በማይችል ሳንቲም እየቸበቸበው ያለው የአገሪቱ ብቸኛ ሃብት መሬት አስመልክቶ ለዜጎችና ለተለያዩ አበዳሪ cover 6ተቋማት የሚቀርበው መረጃ የተሳሳተና ተራ ፕሮፓጋንዳ ላይ የተንጠለጠለ መሆኑንን የሚያጋልጠው ጥናት ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ተመልሶ መታተሙን ያወሳው አኢጋን የመሬት ነጠቃ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ለማካሄድ ለሚፈልጉ ዜጎችና ዓለምአቀፍ ተቋማት ያመች ዘንድ መረጃዎችን ወደ አንድ ቋት ማሰባሰቡን አስታውቋል።
የኦክላንድ ተቋምና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በጋራ ያዘጋጁት ጥናታዊ ጽሁፍ፣ የጋራ ንቅናቄው ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የመለሰው ትርጉም ጥናትና ተመሳሳይ የመሬት ወረራ መረጃዎች ይተላለፉበት ዘንድ (Land Grab –http://landgrabsmne.wordpress.com) የሚባል ብሎግ እንዲሁም በፌስቡክ Land Grab/መሬት ነጠቃ የሚባል መክፈቱን ይፋ አደርጓል። በተለይም ድረገጹ ደረጃው ተሻሽሎ እንደሚቀርብ አመልክቷል።

ከሙስናው በስተጀርባ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


ከኢየሩሳሌም አርአያ

በሕወሐት የተፈጠረው የቀውስ ማእበል አድማሱን እየለጠጠ መሔዱን ተከትሎ «ታማኝ» ሆነው በሙስና ሲያገለግሉ የቆዩትን ጭምር እየበላ እንደሚገኝ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በቀዳሚነት የሚያነሱት በጉምሩክ ቁልፍ ስልጣን የነበረውን የሕወሐት አባል ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስን ሲሆን እንዴትና በማን ወደስልጣን እንደመጣ እንዲሁም ምን-ምን ተግባራት ይፈፅምና ያስፈፅም እንደነበረ ምንጮቹ ሂደቱን እንደሚከተለው ይገልፁታል።tplf rotten apple
ገ/ዋህድ በ1993ዓ.ም ፓርቲው ለሁለት መሰንጠቁን ተከትሎ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ተደረገ። ከጉምሩክ ሃላፊነት በተጨማሪ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተርነት ስልጣን እንዲጨብጥ የተደረገው በአቶ መለስ በተለይ በአዜብ ይሁንታ ጭምር እንደነበረ ምንጮቹ ይጠቁማሉ። ገ/ዋህድ ለዚህ ስልጣን የበቃው ለአቶ መለስ ቡድን በከፈለው መስዋእትነት ሲሆን በክፍፍሉ ማግስት የሙስና ዘመቻ ተከፍቶ እነአባተ ኪሾና ሌሎች እስር ቤት እንዲገቡ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከመስጠት አንስቶ ራሱ ክስ አዘጋጅ፣ምስክርና ፈራጅ..በመሆን የላቀ ሚና መጫወቱን ያስታውሳሉ። በዚህ ተግባሩ የበለጠ ታማኝነቱን በማሳየቱ ከአዜብ በሚሰጠው ቀጥታ ትእዛዝ ሙስናውን ማከናወን መቀጠሉን ምንጮቹ አያያዘው ይጠቁማሉ። በ10ሺህ ቶን የሚገመት ቡና ከአዜብ በተቀበለው ትእዛዝ በህገወጥ መንገድ ከአገር ተዘርፎ የተሸጠበትና ጉዳዩም በፓርላማ ተነስቶ በጠ/ሚ/ሩ «የሌቦቹን እጅ እንቆርጣለን» የሚል አስቂኝ ምላሽ መሰጠቱን ያስታውሳሉ። በተጨማሪ በጉምሩክ ለረጅም አመት በመምሪያ ሃላፊነት ሽፋን የተቀመጠውና የቢሮውን የበላይ ሃላፊዎች በጥብቅ ከመቆጣጠር ጀምሮ እያንዳንዱን የሙስና ተግባር ከጀርባ ሆኖ የሚያስፈፅመው የአዜብ የቅርብ ስጋ ዘመድ ፍትሃነገስት ክንደያ እንደሚጠቀስና ግለሰቡ ቀረጥ ያልተከፈለባቸው 500 ሳተላይት ዲሾች እንዲገቡና በአዜብ በበላይነት ይመራ ለነበረው የዘረፋ ቡድን ለሰባት አመታት በየወሩ 20ሚሊዮን ከቴሌ በህገወጥ መንገድ እንዲዘረፍ ያደረገና በኋላም ከነገ/ዋህድ ጋር ሆኖ በርካታ ሙስናዎችን በዋናነት በማስፈፀም እንደሚጠቀስ ያመለክታሉ።

Tuesday 14 May 2013

የወያኔ ኢህአዲግ ሥርዓት እና በስደት የተቋቋሙት የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት


ቀን 13/05/2013

የወያኔ ኢህአዲግ ሥርዓት የሃገር ውስጥ አልበቃ ብሎት በስደት ሃገር የተቋቋሙትን የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ አብያተ ክርስቲያናትን በጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት ሥር ለማዋል የሚያደርገው ጥረት።

በአውሮፓ ውስጥ አንጋፋ የምትባለውና ከፍተኛ እድገት በማሳየት የምትታወቀው ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በከፍተኛ ሁከትና ረብሻ ውስጥ እንደምትገኝ በተለያዩ ድህረገጾች ላይ ከሚወጡ መረጃዎች ለመረዳት ችለናል።
London Ethiopian Orthodox Church
ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን
ጉዳዩን ቀረብ ብለን እንደተረዳነው በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ቢቻል በሰላምና እርቅ፤ ካልሆነም ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ ሕጋዊ ባለቤት የሆኑት አባላቷ በነፃነት ተወያይተው በሚያስተላልፉት ውሳኔ እልባት ሊያገኝ በቻለ ነበር። ይህ ሁሉ ተሞክሮ ካልተሳካ ደግሞ የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ቤተ ክርስቲያኗ የምትገኝበትን ሃገር ሕግ ተከትሎ ችግሩ እልባት ማግኘት ሲገባው የዚህ ሁሉ ችግር ምንጭ የሆኑትና ስልጣንን የሙጥኝ ብለው አለቅም ያሉት የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ግርማ ከበደና ደጋፊዎቻቸው የሆኑ ጥቂት ካህናትና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች አብላጫውን የቤተ ክርስቲያኗን አባላት በማግለል ሌሎች ከቤተ ክርስቲያኗ ጋር በአቋም የተለዩ ሆነው በለንደን የሚገኙና በወያኔ አህአዲግ ቀጥተኛ አመራር ሥር ከሚገኙ ከገብረኤልና ከስላሴ አብያተ ክርስቲያናት የተወሰኑ አባላት ጋር በማበር በተለይም አባ ጳውሎስ በትግራይ ተወላጅነት መርጠው የሾማቸው አቡነ እንጦስና ሌላው የትግራይ ተወላጅ የሆኑት መጋቢ ተወልደ ወልደማርያም ጋር እየተመሳጠሩ ብዙ ተንኮልና ሴራ ሲሸርቡ ከቆዩ በኋላ ኢትዮጵያ ካለው ከቤተ መንበረ ፓትርያርክ ጋር በመነጋገር አባላትን ሳያማክሩና ሳያስፈቅዱ ከኢትዮጵያ ጳጳስ በማስመጣት ቤተ ክርስቲያኗ በወያኔ ኢህአዲግ ሹመኞች ቁጥጥር ሥር እንድትውል በመጣር ላይ ይገኛሉ።

Monday 13 May 2013

ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የትግል አንድነት ጥሪ


ሲራጅ ደታንጎ

አዲስ አበባ ዉስጥ በግንቦት 17 ቀን 2005 በሚደረገው ሠላማዊ ሠልፍ የሁሉንም ብሶተኛ ኢትዮጵያዊ ክፍል ጥያቄዎች አንግበን በሙሉ ልብ እንሳተፍ፣ የሕዝቡን አንድነትም ለሚጠራጠሩት ሁሉ በተግባር እናረጋግጥ። በዚህ ወቅት አዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ኅብረት 50ኛ ዓመት፣ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት ከበርካታ የአፍሪካ ሀገሮችና ከአንዳንድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም እንግዶች ስለሚኖሩ፣ የህዝቡን የፍትኅና የመብት ጥያቄዎች ለዓለም ኅብረተሰብ ጭምር ልናሰማ የምንችበት ጥሩ አጋጣሚም ነው እንላለን። አፋኙንና ግፈኛውን መንግሥትም በዓለም ህዝብ ፊት ይበልጥ ለማጋለጥ ያስችለናል።A call for demonstration in Addis Ababa, Ethiopia
ትልቁ አስፈላጊ ተግባር፣ ምላሽ የሚጠይቁት አንገብጋቢ የፍትኅ፣ የመብት (የዕምነት መከበር ጭምር)፣ የህግ የበላይነት፣ … ጥያቄዎች በግልጽና በአንድነት፣ የችግሮቹ ሰለባ በሆነው ህዝብ በራሱ በአደባባይ በሠላማዊ መንገድና በይፋም መገለጻቸው ላይ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በገዥው አምባገነናዊ ቡድን ሙሉ መብቱንና ሠላሙን ጭምር አጥቷል። ህዝቡ ሠላም የሚያገኘው፣ ክብሩንና መብቱን ሊያስመልስ የሚችለው፣ ከእንግዴህ በተባበረና ጠንካራ ትግሉ ብቻ ነው።ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከዓመት በላይ በከፍተኛ ቁርጠኛነትና ብልሃት በግንባር ቀደምትነት ያደሩግት ሠላማዊ ትግል ከእንግዴህ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል አካል እንዲሁን ሁኔታዎች ይጠይቃሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃሳቡን በነፃ የመግለጽ መብቱን፣ የመሠለፍና ጥያቄዎቹን በይፋ የማቅረብ መብቱን ጭምር፣ ዛሬ መልሶ ይቀዳጀው፣ ይጠቀምበትም።

ሙስናን በስንጥር! ከዚያስ?


ዋናዎቹ “ሌቦች” በሞቀው ሆቴላቸው አሉ!!

inter


በቀረጥ፣ በሙስናና ባለስልጣናትን የንግድ ሸሪክ በማድረግ ኢትዮጵያን እየጋለቡዋት ያሉ “ባለሃብቶችና አሽከሮቻቸው” እስካልተነኩ ድረስ ኢህአዴግ በሙስና ላይ የጀመረውን ትግል ሙሉ ሊያደርገው እንደማይችል ተገለጸ። ጅማሮው የችግሩ ቁልፍና እምብርት በሆነው ተቋም ላይ መሆኑ የሚደነቅ እንደሆነ የሚገልጹ ክፍሎች ደግሞ ድሩ ያልተበተበው የለምና የመጨረሻው አካሄድ ወዴት እንደሚያመራ ለመገመት ቢቻልም ጅምሩ ይገፋል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው አስታውቀዋል።
የባለስልጣናት ሚስቶችን፣ ዘመዶችና ወዳጆችን በተቋሞቻቸው ውስጥ በማይመጥኑት ሃላፊነት በመመደብ፣  ከተለያዩ የማማለያ ሽልማቶች ጋር ከፍተኛ ደሞዝ በመክፈል፣ አንዳንዴም ውጪ አገር ድረስ የህክምና ወጪ በመሸፈን ሰበብ የአገሪቱን የአመራር በትር ጨብጠው አገሪቱን እያለቡ ያሉት ወገኖች በይፋ እንደሚታወቁ የሚገልጹ ክፍሎች “አሁን ተጀመረ የተባለውና ይፋ የተደረገው የሙስና ትግል እነዚህን ክፍሎች ብብቱ ስር ይዞ የሚቀጥል ከሆነ ከቀልድ አይዘልም” ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ያስቀምጣሉ።
አትራፊ የሆኑ የህዝብና የአገር ተቋማትን ወደ ግላቸው ያለ ክፍያ፣ ያለ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ በተጭበረበረ ጨረታና አሰራር ወደ ግላቸው በማዞር አቶ መለስ “ተራው ህዝብ” በማለት በሚጠሩት ህዝብ ትከሻ ላይ እንዳሻቸው የሚዘሉትን “የሙስና አባቶችን” መታገል የማይችል የጸረ ሙስና ቀረርቶ ከተራ የፖለቲካ ልዩነት የዘለለ መነሻና መድረሻ ሊኖረው እንደማይችል እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ።
ሰሞኑን የመንግስት፣ የግል መሰል የድርጅት፣ የግል፣ የድረገጽ መገናኛዎች የተቀባበሉት ዜና የፌዴራሉ የጸረሙስናና የስነምግባር ኮሚሽን ይፋ ያደረገው የባለስልጣናት፣ የታዋቂ ነጋዴዎች እንዲሁም ተባባሪና የሙስናው ተዋናይ ናቸው የተባሉ አስራ ሶስት ሰዎች ስም የተጠቀሰበት እስር ነው። ይህንኑ ዜና በማድነቅ ጅምሩን የሚያበረታቱ ክፍሎች በበኩላቸው “ቢዘገይም፣ ችግሩና ንቅዘቱ እንዳለ ያደባባይ ሚስጥር ቢሆንም አሁንም አልረፈደምና ኢህአዴግ ለጀመረው የሙስና ትግል ድጋፍ መስጠት አግባብ ነው” ባይ ናቸው።
ኢህአዴግ “ገምተናል” በማለት ቃል ሳይመርጥ ራሱን ከፈረጀበት የሙስና አዘቅት አንድ ሁለት እያለ ዘመቻ መጀመሩ ሊበረታታ እንደሚገባ የሚጠቁሙ ክፍሎች “በአንድ ጀንበር ተዓምር መጠበቅ ከተራ የማንቋሸሽና ሁሌም የመቃወም አዝማሚያ ላይ የመኖር ያህል ያስቆጥራል። በርካታ ችግሮች ቢኖሩም ጅማሬው ወዴት እንደሚያመራ አይታወቅምና በትዕግስት መከታተሉ የተሻለ ይሆናል” ሲሉ በቀጣይ ርምጃው እየሰፋ እንደሚሄድ ተስፋቸውን ይገልጻሉ። ዜናውን ያቀረበው ኢቲቪን ግን ይወቅሳሉ።

ሰበር ዜና፣ በባህር ዳር ከተማ ከ16 በላይ ሰዎች ተገደሉ



እሁድ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ የአባይን ድልድይ እንዲጠብቅ የተመደበ የፌደራል ፖሊስ አባል እያነጣጠረ ሰዎችን ሲገድል አምሽቷል። የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከ16-18 ንጹሀን ዜጎች ያለምንም ምክንያት ከፌደራል ፖሊሱ በተተኮሱ ጥይቶች ተገድለዋል።
የፌደራል ፖሊሱ እያነጣጠረ ንጹሀን ዜጎችን ሲገድል በአቅራቢያው የነበሩ የብአዴን ጽ/ቤት ጠባቂዎች እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥበው እንደቆዩ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
የብአዴን ጽ/ቤት ጠባቂዎች በግለሰቡ ላይ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ የዜጎችን ህይወት ሊታደጉ ሲገባቸው ይልቁኑም ሰውየውን ለመያዝ በመፈለግ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ ግለሰቡ ያገኘውን ሰው እየተኮሰ ሲገድል እንደነበር በአቅራቢያው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል።
ሁኔታው በባህር-ዳር ከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ መረበሽ መፍጠሩ ታውቋል። የከተማው ነዋሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የተካሄደውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለማውገዝ እንደሚፈልጉም ዜናውን ያቀበሉን የባህር-ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ኢሳት (የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በበኩሉ ዜናውን እንዲህ ዘግቦታል)

የህዝብ አስተያየት፣ የሙስና እስርን አስመልክቶ


ሰሞኑን በወያኔዎች ቤት ብዙ ነገር እየሰማን ነው ። በተለይ ከሙስና ጋር በተያያዘ ጉዳይ ። ነገር ግን በዚህ ሙስና በሚባለው ጉዳይ የሚሰራ አንድ ድርጅት አለ ” ጸረ ሙስና ” የሚባለው ማለት ነው ። ይህ መስሪያ ቤት ከወያኔ የፋሽስት ስርዐት ለማፈንገጥ የሚሞክሩን ወይም ከዚህ የማፊያ ቡድን የተለየ ሃሳብ አመጣለሁ ለሚሉትን ወደ ከርቸሌ መወርወሪያ መስመር ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው የወያኔ ባለስልጣን ሆኖ በሙስና ያልተዘፈቀ የለም ። ይህም መረጃ በጸረ ሙስና ቢሮ እጅ ይገኛል ። ወያኔ ማሰር ሲፈልግ በስልጣን እያሉ የተጨማለቁበትን የሙስና ጉዳይ መዘዝ በማድረግ ግለሰቦቹን ለማሸማቀቅ ብሎም ሌሎች ሙሰኞችን አድርጉ የተባሉትን ህሊናቸውን ሺጠው ህዝብን ማሰቃየትን ሳያቅማሙ እንዲቀጥሉ ለማስጠንቀቅ የተመሰረት መስሪያ ቤት ነው ። ይህ “ጸረ ሙስና “የሚባለው መስሪያ ቤት እንደ ስሙ ቢሆን አፈ ጉባኤው አባዱላ ገመዳ ታራሚ መሆን ሲጠበቅበት ለሙስና ክስ ምስክር ይሆን ነበር??? ሌላው የሙስና እናት አዜብ መስፍን እያለች ባጃጅ ሙሰኞች ቀድመው ይያዙ ነበር??? ለነገሩ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም የዘራውን ያጭዳል ! ለሁሉም ጊዜ አለው! Yessuf Abdo (Facebook)
የባለስልጣናት ሚስቶችን፣ ዘመዶችና ወዳጆችን በተቋሞቻቸው ውስጥ በማይመጥኑት ሃላፊነት በመመደብ፣ ከተለያዩ የማማለያ ሽልማቶች ጋር ከፍተኛ ደሞዝ በመክፈል፣ አንዳንዴም ውጪ አገር ድረስ የህክምና ወጪ በመሸፈን ሰበብ የአገሪቱን የአመራር በትር ጨብጠው አገሪቱን እያለቡ ያሉት ወገኖች በይፋ እንደሚታወቁ የሚገልጹ ክፍሎች “አሁን ተጀመረ የተባለውና ይፋ የተደረገው የሙስና ትግል እነዚህን ክፍሎች ብብቱ ስር ይዞ የሚቀጥል ከሆነ ከቀልድ አይዘልም” ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ያስቀምጣሉ። ጎልጉል

Saturday 11 May 2013

የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣን ዋና እና ምክትል ዳይሬክተሮችን ጨምሮ 16 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ


ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ቀደም ሰል የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩትና ሚኒስቴሩ በበለስልጣን መስሪያ ቤት ሆኖ ሲዋቀር ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ መላኩ ፋንታ፣ ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ወልደዋህድ ገብረጊዮርጊስ እና ሌሎች ከ 10 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስና ተጠርጥረው እንደሆነ መንግስት ገልጿል።
የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜና አቅራቢ አጠቃላይ የታሰሩት ሰዎች 12 መሆናቸውን ሲገልጽ፤ዝርዝር ዜናውን ያነበበው ሪፖርተር ታሳሪዎቹ 16 መሆናቸውን ነው በዘገባው ያቀረበው።
ሁለቱን ባለስልጣናትና ከነሱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉት ሰዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ክስ የመሰረተውም፤የፌዴራሉ የጸረ ሙስና ኮሚሽን እንደሆነ ተመልክቷል።
ከሁለቱ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረጉት ግለሰቦች እሸቱ ወልደሰማያት – በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፣ አስመላሽ ወልደማሪያም- የቃሊቲ ጉምሩክ ኃላፊ ፣ ጥሩነህ በርታ- በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቡድን መሪ ፣ አምኘ ታገለ- የናዝሬት ጉምሩክ ኃላፊ ፣ ሙሉጌታ ጋሻው- በኦሮሚያ ልዩ ዞን መሀንዲስ ፣ ከተማ ከበደ- የኬኬ ትሬዲንግ ባለቤት ፣ ስማቸው ከበደ- የኢንተርኮንቴንታል ሆቴል ባለቤት ፣ምህረት አብ አብርሀ- ባለሀብት፣ነጋ ገብረእግዚአብሄር- የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት ፣ ዘሪሁን ዘውዴ -ትራንዚተርና ደላላ ፣ማርሸት ተስፉ – ትራንዚተርና ደላላ ናቸው፡፡
ኮሚሽኑ ባለስልጣናቱን እና ሌሎቹን ግለሰቦች  በፖሊስ ስር እንዲውሉ ያደረጋቸው ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ነው ተብሏል።

Friday 10 May 2013

ሲጠበቅ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ ዛሬ ተካሄደ


ክራንቻ፣ ከደቡብ አፍሪካ

በዛሬው ዕለት የተደረገውን ሰልፍ ለማደናቀፍ የወያኔ መንግስት ጭፍሮች ለዲፕሎማቶች እና ለፖሊስ የሰጡት የሀሰት ውንጀላ በትላንትናው ዕለት ውድቅ ተደርጎ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል።
ተቃዋሚ ሀይሎች የሚያደርጉትን የሰላማዊ ሰለፍ እጅግ የፈራው ወያኔ ሰልፉን የጠሩት አሸባሪዎች ናቸው፣ ከዚህ በፊትም ቴዎድሮስ የሚባለውን የኢትዮጵያ ባለስልጣን በደርባን ርዕሰ ከተማ የጠለፋ ሙከራ ሊያካሂዱበት ነበር የሚልና መሰል የሀሰት ውንጀላዎችን በመደርደር ቢሟገትም ጉዳዩ የሚመለከተው አካል የደቡብ አፍሪካን ዲሞክራሲያዊ ህገ-መንግስት የሚጻረር ስህተት ላለመፈጸም ሲል የሰላማዊ ሰልፉን ፈቃድ በደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሰጥቷል።
በመሆኑን ዛሬ አርብ ሜይ 10፣ 2013 ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በጆሀንስበርግ የተሰበሰበው ህዝብ ወደ ፕሪቶሪያ ጉዞውን በማድረግ የስብሰባው ስፍራ ተገኝቶ መልዕክቱን በቃልና በደብዳቤ ለተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ልዑክ እና ለደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ቃል-አቀባይ፣ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ተወካይ አቶ ደረጀ አማካኝነት አስረክቧል።
ሌላው በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የተፈጠረ አስገራሚ ነገር ቢኖር፣ የኦጋዴን ተቃዋሚ ሀይሎች በስፍራው በመገኘት “ከወያኔ እንጂ ከኢትዮጵያ ህዝብ የመገንጠል ሀሳብ የለብንም… ወያኔ ይወገድ!” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከ ኦጋዴን ወገኖቻችን መካከል አንዲት እህታችን ይዛ የነበረው መፈክር የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ነበር። እንዲህ ይነበባል፣

“60% OF ETHIOPIAN GPD IS WESTERN AID TO KILL CIVILIANS”

ድል ለሰፊው ህዝብ!

Wednesday 8 May 2013

Ethiopia: Loss of Li ves and Displacement Due to Border Disp ute in Eastern Ethi opia


HRLHA FineHRLHA UrgentAction
May 7, 2013
The Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA) would like to express its deep concern over the negligence of both the federal and regional governments in Ethiopia regarding the violence that has been going on for about six months against the Oromos in Eastern Hararge Zone of Oromia Regional State.
According to reports obtained by HRLHA from different sources, this government-backed violence that has been going on in the name of border dispute around the Anniya, Jarso and Miyesso districts between the Oromia and Ogaden regional states has already resulted in the death and/or disappearance of 37 Oromo nationals and the displacement of about 20,000 others. Around 700 different types of cattle and other valuable possessions are also reported to have been looted.