Tuesday, 15 July 2014

ሰበር ዜና - የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከእንግሊዝ ለኢትዮጵያ ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ (የእንግሊዝ መንግሥትንም ጨምሮ) ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ቅድምያ መስጠታቸውን እና አለመስጠታቸውን በሚያጣራ መልኩ ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግ አዘዘ



ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (ሁማን ራይት) ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ባሰራጨው ዜና  የእንግሊዝከፍተኛው ፍርድ ቤት ከእንግሊዝ ለኢትዮጵያ  ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ (የእንግሊዝ መንግሥትንም ጨምሮ)ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ  መብት ይዞታ ቅድምያ መስጠታቸውን እና አለመስጠታቸውን በሚያጣራ መልኩ ሕጋዊ ምርመራእንዲደረግ ያሳለፈውን ውሳኔ  ''ጠቃሚ እርምጃ'' በማለት አሞካሽቶታል።
ውሳኔው በተለይ በቅርቡ ከአርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ መታገት በኃላ የእንግሊዝ መንግስት  ''የባህር ማዶ የልማት ትብብርድርጅት'' (UK Department for International Development (DFID) ) ለኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ ድጎማሊያደርግ የነበረ ከመሆኑ አንፃር የዛሬው ውሳኔ ከፍተኛ መልዕክት ማስተላለፉ አይቀርም።በሌላ በኩል የዛሬው የፍርድቤቱውሳኔ ይሄው የልማት ድርጅት (DFID) በበቂ ሁኔታ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ ይዞታ ጉዳይ አለመመርመሩን ጠቁሞ በእዚሁአዲሱ የፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግበት ማዘዙን ያብራራል።

የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእርምጃውን ፋይዳ ሲያስረዳ  የድርጅቱ የአፍሪካ ክፍል ተጠሪ የተናገሩትንበመጥቀስ ነው።እንዲህ ይነበባል -

''
የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድቤት ውሳኔ ለሌሎች መንግሥታት እና እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የማንቅያጥሪ ነው።ምክንያቱም ሀገራትም ሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚሰጡትን የልማት ፕሮግራም ሁሉ ቅድምያ ከሰብዓዊይዞታ አንፃር እንዲመለከቱ ያደርጋል''ይላል።

የዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (ሁማን ራይት) ስለ እንግሊዙ ከፍተኛ ፍርድቤት የዛሬ ውሳኔ አስመልክቶያወጣውን ዘገባ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።

Ethiopia: UK Aid Should Respect Rights
Ruling Permits Review of Development Agency’s Compliance
JULY 14, 2014
(London) – A UK High Court ruling allowing judicial review of the UK aid agency’s compliance with its own human rights policies in Ethiopia is an important step toward greater accountability in development assistance.

Thursday, 10 July 2014

ከንግድ ባንክ መጠኑ ያልተገለጸ ገንዘብ መጥፋቱ ተጠቆመ

 ‹ተሰርቋል ሳይሆን የሆነው ነገር ሌላ ነው›› የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፊንፊኔ ቅርንጫፍና ከዋናው መሥሪያ ቤት ፋይናንስ መቆጣጠሪያ፣ መጠኑ ያልተገለጸ ገንዘብ መጥፋቱን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምንም የጠፋም ሆነ የተሰረቀ ገንዘብ እንደሌለ፣ ነገር ግን አንድ የባንክ ሠራተኛ በቁጥጥር ሥር ውሎ የባንኩ ትራንዛክሽን እየተመረመረ መሆኑን ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለይ የፊንፊኔ ቅርንጫፍ ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ መሰረቁን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ የባንኩን አሠራርና ሲስተም በደንብ በሚያውቁና ከሌሎች ሠራተኞች የተሻለ ደረጃና ዕውቀት ባላቸው ገንዘቡ በተለያየ ዘዴ መውጣቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ የባንኩ የበላይ ኃላፊዎች ጉዳዩን በሚስጥር ይዘውና የተወሰኑ ሠራተኞች እንዲታሰሩ በማድረግ በምርምራ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በተለያዩ ቅርንጫፎች ከአንዱ ሒሳብ ወደ ሌላኛው በማንቀሳቀስና በሐሰተኛ ሰነድ ሒሳብ በመክፈት የተለያዩ ስርቆት የሚፈጸም ቢሆንም፣ አሁን አሁን ግን ረቀቅ ባለ ዘዴ ጠቀም ያለ ገንዘብ እየተወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ይኼ የሚሆነው ልምድ ያላቸው ሠራተኞች ባልጠበቁትና ባልገመቱት ሁኔታ ከኃላፊነታቸው እየተነሱ ልምድ የሌላቸውና በቅርብ ጊዜ ቅጥሮች እየተተኩ በመሆኑ፣ ሌሎቹም ‹‹ነገ የምነሳ ከሆነ ለምን ዛሬ አልጠቀምም?›› በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ የወንጀል ድርጊቱን ለመፈጸም ሳይነሳሱ እንዳልቀሩ ምንጮቹ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡
ሌላው ምንጮች የሚጠቁሙት ነገር ቢኖር ቄራ አካባቢ ከሚገኘውና በአገሪቱ ያሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች (832 ናቸው) ሒሳብ የሚወራረድበት ከዋናው መሥሪያ ቤት ፋይናንስ መቆጣሪያ፣ መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ መጥፋቱን ነው፡፡ በሚስጥር የተያዘው የዚህ ገንዘብ መጥፋት ውስጥ ለውስጥ እየተጣራ መሆኑንና ወደ ሌላ ክልል ቅርንጫፎች ገንዘቡን አስተላልፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ሁለት ሠራተኞች መታሰራቸውን ጠቁመዋል፡፡