Tuesday 11 November 2014


OMN: Interview With Amnesty International Researcher Claire Beston, November 10, 2014

Monday 10 November 2014

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ከፍተኛ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ የነበሩት ረዳኢ ገ/አናኒያ ከስልጣናቸው ተነሱ

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ከፍተኛ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ የነበሩት ረዳኢ ገ/አናኒያ ከስልጣን መነሳታቸውን ምንጮች አስታወቁ። የሕወሀት አባል የሆኑት ረዳኢ ከ1985ዓ.ም ጀምሮ የክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ሃላፊ በመሆን በመቶ አለቃ ማዕረግ እስከ 1993ዓ.ም ደረስ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ፓርቲው ለሁለት ሲሰነጠቅ በመለስ ዜናዊ ታማኝ ሆነው ከተመረጡት አንዱ የሆኑት ረዳኢ በፌዴራል የልዩ ተወርዋሪ ሃይል ሃላፊ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮቹ አስታወሰዋል። ቀጥታ ተጠሪነታቸው ለጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንደነበር ሲታወቅ በመቀጠል የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ ተደርገው ተሾሙ። በ1997-98 በዜጎች ላይ ለደረሰው የጅምላ ግድያና እስር እንዲሁም ስቃይ ከመለስ ትእዛዝ በመቀበል ሲያስፈፅሙ የነበሩት ረዳኢ መሆናቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።
በበርካታ ሰላማዊ ወገኖች ላይ ተመሳሳይ ግፍ ያስፈፅሙ እንደነበረ አክለዋል። ረዳኢ በ10 ሚሊየን የሚቆጠር ሃብት በሙስና እንዳከማቹ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። ከስልጣን የተነሱት ለመለስ ታማኝ ስለነበሩ ነው ብለዋል ምንጮቹ። ረዳኢ ወደ አሜሪካ ለመምጣት ሃሳብ እንዳላቸው እዚህ ከሚኖሩ የቅርብ ወዳጃቸው የተገኘው ጥቆማ ያመለክታል።

ሌ/ጄነራል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ሊወጡ ሲሉ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በደህንነቶች ተመለሱ

November11,2014

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ጄ/ል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ለመውጣት ሲሉ ከቦሌ አየር ማረፊያ በደህንነቶች እንዳይወጡ መደረጋቸውን ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል።
ከመከላከያ የጦር አዛዥነታቸው በጄ/ል ሳሞራ የኑስ እንዲነሱ የተደረጉት ጄ/ል አበባው ከአገር እንዳይወጡ የተደረገበት ምክንያት ግልፅ እንዳልሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የተለያዩ ጥያቄዎች እንዳሉ በመግለፅ ለኢታማጆር ሹሙ ጄ/ል ሳሞራ ከረር ያለ ሪፖርት ያቀረቡት ጄ/ል ሰዓረ፣ ጄ/ል ሞላና ጄ/ል አበባው መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ በሳሞራ የተሰጠው መልስ « የትምህክተኞች ጥያቄ ነው፤ ችግር የለም..» የሚሉና ጥያቄዎቹን የሚያጣጥሉ እንደነበሩ አስታውሰዋል።

ሶስቱ ጄኔራሎች በሳሞራ ምላሽ በመበሳጨት ከስልጣናቸው ለማስነሳት በምስጢር ቢመክሩም መረጃው ባልታወቀ መንገድ አፈትልኰ ጄ/ል ሳሞራ ዘንድ በመድረሱ ጄ/ል ሰዓረ ከሰሜን ዕዝ አዛዥነታቸው፣ ጄ/ል ሞላ ከአየር ሃይል እንዲሁም ጄ/ል አበባው ከያዙት ስልጣን በሳሞራ በአስቸኳይ እንዲነሱ ሲደረግ በተለይ ጄ/ል አበባው ከ2 ወር በፊት ከመከላከያ እንዲባረሩ መደረጉን ምንጮቹ አስረድተዋል። በጄ/ል ሰዓረ ቦታ ጄ/ል ገብራት አየለ ሲተኩ በጄ/ል ሞላ ደግሞ የአግአዚ ክ/ሰራዊት አዛዥ ጄ/ል አደም መሐመድ መተከታቸውን አስታውቀዋል።
ሁለቱ ጄኔራሎች ዝቅ ባለ ደረጃ ተራ የመምሪያ ሃላፊ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮቹ ገልፀዋል። ጄኔራል የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የጠ/ሚ/ሩ እንደሆነ ህገመንግስቱ ቢደነግግም ነገር ግን የተጠቀሱት ጄኔራሎች የተነሱት በጄ/ል ሳሞራ ትእዛዝ፣ የተተኩትም በሳቸው ውሳኔ እንደሆነና ጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም ከወራቶች በኋላ እንዲያውቁ ተደርጐ ለተሾሙት ጄኔራሎች የማእረግ እድገት እንዲሰጡ መደረጉን ምንጮቹ አስረድተዋል። ጄ/ል አበባውና ጄ/ል ሰዓረ በሙስና ከተዘፈቁ የጦር አዛዦች እንደሚጠቀሱ አክለው ገልፀዋል። ..ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ከፍተኛ ግመገማ ከሰሞኑ እየተካሄደ ሲሆን ስር የሰደዱ ቀውሶች እየፈነዱ መሆኑ ታውቋል።

ኢትዮጵያ የመብት ጥሰት እንድታቆም መጠየቁ

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ። በደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ አንጎላዊው ጋዜጠኛ ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች መፍታት አለበት ብሏል።

Rafael Marques
ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ አንጎላዊ ጋዜጠኛ ነው። በሙያው በሃገሩ አንጎላ በርካታ ክስ እና እስር እንደገጠመው ይነገራል። ባለፈው ወር በደቡብ አፍሪካ ዊትስ በተካሄደው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽን ጨምሮ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ጥሰት በመፈጸም ከአፍሪካ ህብረት ህልም በተቃራኒ ቆማለች በማለት ተችቷል። ''የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በቀዳሚነት የመላ አፍሪካውያንን ህልም ይወክላል። የሰው ልጅ ክብር እና የሰብዓዊ መብት ክብር ደግሞ የሁሉም አፍሪካውያን የጋራ ህልም ነው። ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የሰዎችን ሰብዓዊ መብት በመጣስ በተቃራኒው መንገድ እየተጓዘች ነው። ይህ ደግሞ የአፍሪካውያንን ህልም አይወክልም። የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በመፍታት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነትን እንዲያከብር እና ዜጎች እና ጋዜጠኞች ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን በተግባር እንዲያውሉ እንዲፈቅድ የአፍሪካ ህብረት ጫና ማድረግ ይኖርበታል። ''

አቶ በረከት ስምዖን ያስገቡትን የስልጣን ጥያቄ ሕወሓቶች እንዳልተቀበሉት ተነገረ; “እለቃለሁ የሚል ከሆነ ሃብቱ መመርመር አለበት” ተብሏል

አቶ በረከት ስምዖን ያስገቡትን የስልጣን ጥያቄ ሕወሓቶች እንዳልተቀበሉት ተነገረ; “እለቃለሁ የሚል ከሆነ ሃብቱ መመርመር አለበት” ተብሏል

Bereket Simon weeping with his wife over Meles Zenawi's death

ምንሊክ ሳልሳዊ
-በውሳኔው የማይስማማ ከሆነ በሱና በቤተሰቡ በወዳጆቹ ስም የተመዘገበው ሃብት እንዲጣራ ተብሏል::
-ሳያገግሙ ስብሰባ እንዲመራ እና ሚዲያ ላይ እንዲቀርብ ታዟል::
የብአዲን/ኢሕአዲግ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡት የስልጣን መልቀቂያ ለጊዜው በሚል ውድቅ መደረጉን ሆኖም በቅርቡ መልስ ይሰጥበታል ሲሉ የሕወሓት ባለስልጣናት መመለሳቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::አብዛኛውን ጊዜ ራሳቸውን ከቤት በማስቀመጥ እና በማዝናናት ያሳልፋሉ የተባሉት አቶ በረከት ስምኦን በልባቸው ላይ በተገጠመላቸው አርቴፊሻል መሳሪያ በጤንነታቸው ላይ ከባድ እክል እንደፈጠረባቸው እና ከወራት በፊት ሳኡድ አረቢያ ታክመው ቢመጡም ሊሻላቸው እንዳልቻለ እንዲሁም ባለፈው ሳምንት በድጋሚ ቢሄዱም ሆስፒታሉ ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ሲታወቅ ከሕክምና መልስ ወደ ቢሯቸው የገቡት በጣት የሚቆጠር ቀናት እንደሆነ ታውቋል::
ይህን ሰሞን ስብሰባ መምራት አለብህ በሚዲያ መታየት አለብህ የሚል ግዳጅ ከሕወሓት ባለስልጣናት ወርዶላቸው የተደናበሩት አቶ በረከት ማገገም እንኳን ሳይችሉ በስራ መደራረብ እንዲሞቱ እየተደረገ ነው ሲሉ ከቤተሰባቸው አንዱ የሆኑት ሲናገሩ ተሰምቷል::አቶ በረከት በከፍተኛ ህመም ውስጥ እንዳሉ ሲታወቅ የሕወሓት ባለስልጣኖች የአዜብን ቡድን እንደመቱት ወዲያው በረከትንም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ አሽቀንጥረው ካሳንቺስ አዲስ ቢሮ እንደሰጡት ሲታወቅ መገፋቱ እያንገበገበው በሽታውን እንዳባባሰበት ታውቋል::

Sunday 9 November 2014

ዶ/ር መረራ ጉዲና፡- ኢሳት ጠመንጃ የለውም፣ የትጥቅ ትግልም እያካሄደ አይደለም

የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ “በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን የፖለቲካ እንቅስቃሴ” በተመለከተ አሜሪካ ውስጥ ላለፉት ስድስት ወራት ጥናት ሲያደርጉ ቆይተው በቅርቡ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ በአሜሪካ ስለነበራቸው ቆይታ፣ ስለ ጥናታቸው፣ እንዲሁም በሃገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ከአዲስ አድማስ ከፍተኛ ሪፖርተር አለማየሁ አንበሴ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ እንዲህ ቀርቧል፡፡
አለማየሁ አንበሴ፡- ላለፉት ስድስት ወራት አሜሪካ ቆይተው ነው የመጡት፡፡ የጉዞዎ አላማ ምን ነበር?
ዶ/ር መረራ ጉዲና፡- “ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዲሞክራሲ” በተባለ የአሜሪካ ተቋም ውስጥ ጥናት ሳደርግ ነው የቆየሁት፡፡ ዲሞክራሲ እና የኢትዮጵያ ዳያስፖራን በተመለከተ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረገው ዲሞክራሲያዊ ትግል ውስጥ ያላቸውን ሚና ማየት ነበር የጥናቱ ዓላማ፡፡ የአሜሪካ ዋና ከተማ ዲሲ ውስጥ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ዋና ከተማ በሚመስል ደረጃ ነው ኢትዮጵያውያኖች ያሉት፡፡ እዚያ አካባቢ ፖለቲካው ያገባናል ብለው የሚንቀሳቀሱትን አግኝቻለሁ፡፡ እንደ ሲያትል፣ ሳንዲያጎ፣ ላስቬጋስ፣ ሳንፍራንሲስኮ፣ ሚኒሶታ፣ ዳላስ፣ ፊላደልፊያ በመሳሰሉት የአሜሪካ ከተሞች ተዛዙሬም ኢትዮጵያውያንን አነጋግሬያለሁ፡፡ በዚያውም ለፓርቲያችን ድጋፍ ለማሰባሰብ ሞክሬያለሁ፡፡ ከሞላ ጎደል በውጭ ያለው ዳያስፖራ በሀገሩ ፖለቲካ ላይ እንዴት ነው? የሚለውን ነው ያየሁት፡፡ በ“ኢሳት” እና በ“ቪኦኤ” እንዲሁም በ“ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ” ላይ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በተመለከተ በስፋት ቃለምልልሶችንና ክርክሮችን ለማድረግ ሞክሬያለሁ፡፡ መጨረሻ ላይም አሜሪካውያንና ኢትዮጵያውያን በተገኙበት መድረክ ላይ የጥናት ውጤቱን አቅርቤአለሁ፡፡
አለማየሁ አንበሴ፡- መሰረታዊ ችግሮቻችንን ለመፍታት ከኢትዮጵያ መንግስት፣ በውጭው ዓለም ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ምን ይጠበቃል በሚሉት ሶስት መሰረታዊ ነገሮች ላይ ነው አስተያየት ለማቅረብ የሞከርኩት፡፡Photo - Merera Gudina
ዶ/ር መረራ ጉዲና፡- በወቅቱ ፕሬዚዳንት ኦባማ፣ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችን ሰብስቦ ሲያነጋግር፣ እኔ ጥናት ያቀረብኩበት ዲሞክራቶች የሚመሩት ናሽናል ዲሞክራቲክ ኢንስቲቲዩት፣ እንዲሁም ዊልሰን ሴንተርና ፍሪደም ሴንተር የሚባሉ ተቋማት በጋራ የአፍሪካ ሲቪል ማህበረሰብ አባላትን ሰብስበው ነበር፡፡ በጣም ሰፊ ስብሰባ ነው፡፡ በመድረኩ ላይም ስለ አፍሪካ መሰረታዊ ችግሮች ማለትም ስለ ምርጫ፣ ስለ ፍትህ፣ ስለ ሰብአዊ መብት አከባበር… ሃሳቦች ተንፀባርቀው ውይይት ተደርጓል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይም በተናጋሪነት ተሳትፌያለሁ፡፡ እንግዲህ እነዚህን ስራዎች ስሰራ ነው የቆየሁት፡፡
አለማየሁ አንበሴ፡- በዳያስፖራው ላይ ባካሄዱት ጥናት ምን ውጤት አገኙ?