Friday 29 August 2014

ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለኤርትራ ለመሸጥ መዘጋጀቷ ተሰማ


ኢትዮጵያ በተዘዋዋሪ መሸጡ አያሳስበኝም አለች
የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ ለመግዛት ከተስማማው አንድ መቶ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ መጠኑ ይፋ ያልተደረገ ኃይል ለኤርትራ ለመሸጥ ዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡
የሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ ኩባንያን ዋቢ ያደረገው ኢነርጂ ቢዝነስ ሪቪው ድረ ገጽ ባስነበበው ዘገባ መሠረት፣ በምሥራቃዊ ሱዳን በኩል ከከሰላ ግዛት ተነስቶ ወደ ኤርትራ የሚዘረጋ የ45 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር መዘርጋት ተጀምሯል፡፡
ከሁለት ዓመት በኋላ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የህዳሴው ግድብ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ግብፅና አሁን ደግሞ ኤርትራ ተጠቃሚ ይሆኑበታል ተብሎ ስድስት ሺሕ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ባለፈው ዓመት ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ተሻጋሪ ኃይል ማሰራጫ መስመርን በጋራ ማስመረቃቸው የሚታወስ ነው፡፡
ሱዳን ወደ ኤርትራ ልትሸጥ ዝግጅት መጀመሯን በማስመልከት ሪፖርተር ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የኃይል ሽያጭ ስምምነቱ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተደረገ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ ‹‹ይህም ሆኖ ሱዳን ከኢትዮጵያ የገዛችውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማን እንደምታስተላልፍና ከማን ጋር እንደምትነግድ ለመቆጣጠር አንችልም፣ ሉዓላዊነቷም አይፈቅድልንም፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ አስገዳጁን ውል ከግብጽና ሱዳን ጋር ተፈራረመች


ኢሳት ዜና :-የግብጽ ጋዜጦች እንደዘገቡት ኢትዮጵያ ለወራት ውድቅ ስታደርገው የነበረውን ስምምነት ከግብጽ ጋር
ተፈራርማለች። አዲሱ ስምምነት የአባይ ግድብ ግንባታ በውጭ አገር ገለልተኛ አጥኚዎች እንዲጠናና ኢትዮጵያም የጥናቱን ውጤት እንድታከብር የሚያስገድድ ነው።
በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ሲደራደሩ የቆዩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ ከወራት በፊት ሱዳን ላይ ተካሂዶ በነበረው የሰላም ስምምነት ላይ
ግብጽ ግድቡ በውጭ አገር ባለሙያዎች እንዲጠና ያቀረበቸውን አጀንዳ ውድቅ ማድረጓን ገልጸው ነበር። ኢትዮጰያ ግድቡ ከመጀመሩ በፊት በቂ ጥናት እንደተካሄደበት
እንዲሁም ገለልተኛ አካል አጥንቶ ችግር እንሌለበት መግለጹን ስታስረዳ ቆይታለች። ይሁን እንጅ ሰሞኑን በተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ በፊት የያዘቸውን አቋም ቀይራ
በግብጽ አቋም በመስማማት አስገዳጅ ውል ፈርማለች። ውሉ የግድቡ ግንባታ ሳይቋረጥ እንዲካሄድ የሚጠይቅ ሲሆን፣ አዲሱ አጥኚ ቡድን ግድቡ በግብጽ ላይ ችግር ያስከትላል
ብሎ ካመነ ኢትዮጵያ የግድቡን ዲዛይን ለመቀየር ትገደዳለች።
ኢትዮጵያን ይህን አስገዳጅ ውል ለመፈረም ምን እንዳስገደዳት በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

በአዲስአበባ የሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት መዳከም አሳሳቢ ሆኗል


የኢትዮ- ቴሌኮም በአዲስአበባ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማሳደግ የ4ጂ አገልግሎት መስጠት የሚችልበት ደረጃ
ደርሻለሁ ቢልም የአገልግሎቱ ጥራት በከፍተኛ ደረጃ እየወደቀ መምጣቱ ተጠቃሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ምሬት ውስጥ እየከተተ ነው፡፡
በ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ወጪ የቻይናዎቹ ሁዋዌ እና ዜድቲኢ የሚባሉ ኩባንያዎች የማስፋፋፊያውን ፕሮጀክት ለመስራት ከኢትዮቴሎኮም ጋር በዚህ ዓመት መጀመሪያ የተፈራረሙ ሲሆን የአዲስአበባው ፕሮጀክት እስከሰኔ ወር 2006 ዓ.ም መጨረሻ ተጠናቆ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ነበር፡፡ ኢትዮቴሌኮም የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በስኬት ተጠናቋል በሚል ተደጋጋሚ መግለጫ የሰጠ ሲሆን ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሞባይል ሒሳብ ለመሙላትና ቀሪ ሒሳብ ለመጠየቅ አለመቻል፣ የፈለጉትን ሰው በቀላሉ ደውሎ ማግኘት አለመቻል፣ ያልደወሉበት ሒሳብ መቆረጥ፣ የሞባይል ኢንተርኔት በተለይ ፈጣን ነው የተባለውን 3ጂ ጨምሮ ደካማ መሆን፣ የፌስቡክ አካውንት አለመከፈት፣ የገመድ አልባ ኢንተርኔትና ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥና ደካማ መሆን በስፋት እየታየ ነው፡፡
ያነጋገርናቸው ተጠቃሚዎች የአፍሪካ ህብረትና የሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የሆነችው አዲስአበባ ጥራት ያለው የሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት ብርቋ መሆኑ እንደሚያሳዝናቸው ተናግረዋል፡፡ አንድ አስተያየት ሰጪ እንዳሉት ኢትዮቴሌኮም የተሻለ ማስፋፊያ አድርጌለሁ እያለ በተግባር ይህ አለመታየቱ ምናልባትም መንግሥት በተለይ በማህበራዊ ድረገጾች እየተሰነዘረበት ያለውን ጠንካራ ተቃውሞና ትችት ለማፈን የተጠቀመበት አዲስ ዘዴ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንደገባው ተናግሮአል፡፡
የኢንተርኔት ኔትወርክ እንደመብራት ብልጭ ድርግም እያለ ብዙዎች በመበሳጨት አገልግሎቱን እየተው ነው ያለው አስተያየት ሰጪያችን መንግሥት በዚህ ሒደት ከሚያጣው ገንዘብ ይልቅ ተቃዋሚዎቹን ለማፈን ትልቅ ግምት ሳይሰጠው እንዳልቀረ አስረድቷል፡፡

ሰበር ዜና የኢትዮዽያ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሲውዲን አለማቀፍ ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው።

አስራሦስት የኢትዮዽያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የጦር መኮንኖች በሲዊዲን አለም አቀፍ የጦር ፍርድቤት ተከሰሱ።
እነሱም
1-አርከበእቁባይ
2-በረከት ስምሆን
3-አባዱኣ ገመዳ
4-ሳሞራ የኑስ
5-አባይ ፀአዬ
6-አሰፋ
7-ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ
8-አሰን ሺፋ
9-ሙሉጌታ በርሄ
10-ነጋ በርሄ
11-ወርቅነህ ገበየው
12-ኮማንደር ሰመረና አንድ ስማቸው ያልተገለጠ ሰው በግድያ፡ አስገድዶ መድፈር በስቃይ፡ ሰዎችን በማንገላታት፡ በህገወጥ ሁኔታ በማሰር ፡በሙስና ክስ ቀርቦባቸዋል።